የ1977ቱ የአዋሹ የባቡር አደጋ ዓለም ካስተናገደቻቸው አስር አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተባለ

የ1977ቱ የአዋሹ የባቡር አደጋ ዓለም ካስተናገደቻቸው አስር አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተባለ – በዓለማችን ዘመናዊ ወይም ሜካናይዝድ የባቡር ትራንስፖርት በ1820ዎቹ እንደተጀመረ ይነገርለታል፡፡

የባቡር ትራንስፖርት በርካታ አሰቃቂ እና አስከፊ የሚባሉ አደጋዎችንም በታሪኩ አስተናግዷል፡፡

በዚህ የባቡር አደጋ ታሪክ ውስጥ አስከፊ ናቸው የተባሉ አስር አደጋዎችም ይፋ ተደርገዋል  ከእነዚህ አደጋዎችም ውስጥ በ 1977 ዓ.ም በአዋሽ የደረሰው የባቡር አደጋ አንዱ ነው ተብሏል ፡፡ ዝርዝሮቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

  1. አል አያታ ባቡር አደጋ – ግብጽ

በፌብርዋሪ 2002 በግብጽ ከካይሮ ወደ ሎግዞር ይጓዝ የነበረ አስራ አንድ ፉርጎ ባቡር በአምስተኛው ፉርጎ በምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ የ 383 ሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት በመሆኑ በባቡር አደጋ ታሪክ በአስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምቷል፡፡

  1. የአዋሽ ወንዝ የባቡር አደጋ – ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ አቆጣጠር በጥር 1977 ከድሬደዋ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረው ባቡር 12 ሜትር ጥልቀት ወዳለው የአዋሽ ወንዝ በመግባቱ 428 ሰዎች ሲሞቱ ከ 500 በላይ ቆስለዋል፡፡ በወቅቱ ባቡሩ ከ1000 በላይ መንገደኞችን ይዞ የነበረ ሲሆን አደጋው ከአፍሪካ እጅግ አሰቃቂው በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ ላይ ተቀምጣል፡፡

  1. ቶሬ ዴል ቢሬዞ የባቡር አደጋ – ስፔን

በጃንዋሪ 1944 በስፔን ሎኔ በተባለ ግዛት የመተላለፊያ ዋሻ ውስጥ አደጋ በደረሰበት ባቡር የሞቱት ሰዎች ቁጥር አከራካሪ ቢሆንም በቅርብ የተካሄዱ ጥናቶች የሟቾቹን ቁጥር እስከ 500 እንደሚደርስ ይጠቁማሉ

  1. የባላቮኖ የባቡር አደጋ – ጣሊያን

ይህ በጣሊያን የደረሰው የባቡር አደጋ በጣሊያን ታሪክ የከፋው እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ አደጋው የደረሰው በማርች 1944 በሌሊት ወቅት መሆኑ ለጉዳቱ ከፍ ማለት ምክንያት ሆኗል፡፡

READ  የኢትዮ-ቴሌኮም አቅርቦትና ፋሲሊቲ ቺፍ በሙስና ተጠርጥረው ተያዙ

ባቡሩ በእንፋሎት ይሰራ ነየበረ ሲሆን በባቡር አደጋው በህገወጥ መንገድ የተጫኑ 426 ሰዎች በካርቦን ሞኖክሳይድ ተበክለው ህይወታቸው አልፏል፡፡

  1. ኡፋ የባቡር አደጋ – ሶቪየት ህብረት

በጁን 1989 የሶቪየት ህብረት ንብረት የሆነው ኡፋ ከተባለው ከተማ 50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይጓዝ የነበረ ባቡር የጫነው የተፈጥ ጋዝ በመፍሰሱ እና ባቡሩ በመቃጠሉ 575 የሚደርሱ ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ በወቅቱ በሶቪየት ህብረት ከደረሱ የባቡር አደጋዎች አስከፊውም ተብሎ ነበር፡፡

  1. ጉዳላጃራ የባቡር አደጋ – ሜክሲኮ

በጃንዋሪ 1915 የደረሰው ይህ የባቡር አደጋ የ 600 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

የአደጋውም መንስኤ የባቡሩ መቆጣጠሪያ መሳሪያ ብልሽት መሆኑ ተነግሮ ነበር፡፡

  1. ባሂር የባቡር አደጋ – ህንድ

በጁን 6 ቀን 1981 በህንድ 800 መንገደኞችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ ባቡር የባጋማንቲ ድልድይን በሚያቋርጥበት ግዜ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዙ በመግባቱ ከ500 እስከ 800 የሚሆኑት ወይም ከዛ በላይ የሚሆኑት አልቃዋል፡፡

  1. ኪዩሪያ የባቡር አደጋ -ሮማንያ

ጃንዊ 1917 የደረሰው ይህ አደጋ ከ800 አስከ 1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለህልፈት የዳረገ ሲሆን ትክክለኛ የአደጋው መንስኬ በውል አልታወቀም፡፡

  1. ሴንት ማይክል ዴ ሞሪኔ የባቡር አደጋ – ፈረንሳይ

ይህ አደጋ የደረሰው  ዲሴምበር 1917 ሲሆን 1000 የፈረንሳይ ወታደሮችን ጭኖ የነበረው ባቡር በገጠመው የመገልበጥ አደጋ ከ 700 በላይ ሰዎች ሞተውበታል፡፡

1.የስሪላንካ ሱናሚ የባቡር አደጋ

በፈረንጆቹ 2004 የደረሰው ይህ አደጋ የአለማችን አስከፊው የባቡር አደጋ ነው የተባለ ሲሆን የ 1700 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡ አደጋው የደረሰው ባቡሩ በህንድ ውቂያኖስ በተነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ በተፈጠረ ሱናሚ መመታቱን ተከትሎ ነበር፡፡

READ  ጎ - ገበያ (GoGebeya) የተባለ ነጻ የኢትዮጵያ የኦንላይን ግብይት አፕሊኬሽን ይፋ ሆኗል - News.et

NO COMMENTS