Connect with us

Ethiopia

ሳውዲ አረቢያ ለመጀመርያ ግዜ ለኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ሰጠች

Binyam G-Kirstos

Published

on

ሳውዲ አረቢያ ለኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ሰጠች

ሳውዲ አረቢያ ለመጀመርያ ግዜ ለኢትዮጵያዊያን እስረኞች ምህረት ሰጠች – የጀርመን ድምጽ እንደዘገበው  እስረኞቹ የሚፈቱበት ጊዜ፤ የነበሩበት ሁኔታና ወደ ሐገራቸዉ የሚጓዙበት መንገድ  እስካሁን ግልፅ አይደለም።

የጀርመን ድምጽ የሪያዱ ወኪል ስለሺ ሽብሩ ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያዉን እስረኞች ምሕረት ስታደርግ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ  ማለቱም በዘገባው ተመልክትዋለ

የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸዉ ከታሰሩ ኢትዮጵያዉን መካከል ለ375ቱ ምሕረት አድርገዋል።

ንጉሱ ምሕረቱን ያደረጉት ከኢትዮጵያዉ ፕሬዝደንት ከሙላቱ ተሾመ በቀረበላቸዉ ጥያቄ መሠረት ነዉ።እስረኞቹ የሚፈቱበት ጊዜ፤ የነበሩበት ሁኔታና ወደ ሐገራቸዉ የሚጓዙበት መንገድ ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም።

 

READ  የበዓል ማግስት ወግ ~ (ቁም-ነገርን :( በፈገግታ :) ) (መላኩ አላምረው በድሬቲዩብ)
Continue Reading

Ethiopia

የኦሮሚያ ከተሞች የሰሞኑ አመጽ እና አንዳንድ ያልተገቡ ክስተቶች

Published

on

የኦሮሚያ ከተሞች የሰሞኑ አመጽ እና አንዳንድ ያልተገቡ ክስተቶች

የኦሮሚያ ከተሞች የሰሞኑ አመጽ እና አንዳንድ ያልተገቡ ክስተቶች፤ መንገድ የሚዘጉ የተቃውሞ ሰልፎች መንግስትን ወይስ መንገደኛን ዒላማ ያደረጉ፡፡
ስናፍቅሽ አዲስ በድሬቲዩብ

ሰሞኑን የኦሮሚያ ከተሞች በተቃውሞ ሰልፍ መልካቸውን ቀይረዋል፡፡ አንዳንድ አካባቢዎች የታዩ የተቃውሞ ሰልፎች ጭብጣቸው መልካም አስተዳደር ነው፡፡

ለምሳሌ ጎሬ ከተማ ትናንት በተካሄደ ሰልፍ የቀድሞውን አውሮፕላን ማረፊያ መልሱንል፣ ጉመሮ ሻይ ተጠቃሚ አላደረገንም አይነት መልዕክት የያዘ ሰልፍ ነበር፡፡

በሌላ በኩል እጅግ ተቃራኒ ነገርም ተመልክተናል፡፡ ለምሳሌ ክቡር አቶ ለማ መገርሳና ካቢኔአቸው የሚያወግዘው ኦነግ ባንዲራው የሰልፍ ማድመቂያ በሆነበት ሰልፍ ላይ ለማ መገርሳ የእኛ ነው የሚል መፈክር የሚያሰሙ ሰልፈኞች ታይተዋል፡፡

የነቀምት፣ ወሊሶ እና ሻሸመኔ ሰልፎች ከሌሎች ለየት ባለ መልኩ የተካሄዱ ናቸው፡፡ ትንሽሽ ከተሞች የሚታዩት ሰልፎችም ቢሆኑ ብዙ ወጣቶች ታይተውባቸዋል፡፡

እንደ ጎጃም በር በሚገኙ ከተሞች የሚካሄዱ ሰልፎች ደግሞ ዓይነታቸው ተለይቶብኛል፡፡ የሰልፉ ዓላማ፣ የሰልፉ መሪ፣ የሰልፉ መድረሻ ምን እንደሆነ የሚነግረን አጣን

የሚሉ ወገኖች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ድንጋይ ለመወርወርም ቢሆን የዕለቱ ጉርስ ያስፈልጋል፡፡

በምዕራብ ሀረርጌ እና በምሥራቅ ሀረርጌ ዞን የሚካሄዱ ሰልፎች እንደ እህል መጋዘን ተከዝኖ መቀመጥ ያማይችለውን የጫት ምርት ከገበያ አራርቀውታል፡፡ ከዚህ የሚገኘው ገቢ የአርሶ አደሩ ህልውና ቢሆንም ቄሮዎች ግን አንዲትም ጫት ወደ ገበያ አትወጣም አይነት ዘመቻ ላይ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በፍቼ፣ ሰላሌ፣ ጎሃ ጽዮን በመሳሰሉ ከተሞች የሚካሄዱ ሰልፎች ከአባይ ማዶ የሚመጡ ተሸከርካሪዎች እንዳያልፉ የማድረግ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ ትናንት በርካታ መኪኖች ደጀን ለመቆም ተገደዋል፡፡

መንግስትን እንቃወማለን የሚሉ ወገኖች መንገደኛን ማለፊያ ካሳጡ በእርግጥም የዚህ ሰልፍ ጠሪ ማነው ብለን እንድንጠይቅ እንገደዳለን፡፡

READ  ግሸን መድሀኒት ቤት አበረታች መድኃኒት አስመልክቶ ዘጋርዲያን የተባለው ጋዜጣ የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ላወጣው ዘገባ ምላሽ ሰጠ

ጎሃ ጽዮን አካባቢ ትናንት የህዝብ ማመላለሻዎችን በማስቆም መንገደኛውን ገንዘብ አምጡ ሲሉ የተደመጡ ዱርዬዎች ተገን ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፉን ነው፡፡ በዚህ መልኩ መቀጠል የለበትም፡፡

ሁሉም አካባቢ ለወንጀለኞችና የህዝብን ሰላማዊ ተቃውሞ ተገን አድርገው ወንጀል መፈጸም ለሚሹ አጭበርባሪዎች ሽፋን እንዳያገኙ ነቅቶ መጠበቅ አለበት ብዬ አስባለሁ፡፡

ሁሉም ነገር በማስተዋል ካልሆነ በመጨረሻ ማንም የማያሸንፍበት፤ ሁላችንም የምንጎዳበት ባለቤቱ ያልታወቀ ሀሳብ ውጤት የሆነ ቀውስ ላይ እንወድቃለን፡፡

መንግስትን መቃወም ግለሰቦችን ዋስትና ካሳጣ እና ሰርቶ መግባት አበሳ ከሆነ ትርፋችን ምን እንደሆነ አስረዱኝ፡፡ እንወያይበት፡፡ DIRETUBE

 

Continue Reading

Education

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ወጣ

Published

on

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ወጣ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ወጣ | ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ደረጃውን አስጠብቋል

የትምህርት ሚኒስቴር 35ኛውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ በአሶሳ አካሂዷል፡፡ በየዓመቱ በሚካሄደው ጉባኤ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመታዊ አፈጻጸም እና የቀጣዩ ዓመት እቅዶች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

ይህ ጉባኤ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎችን በትውልድ በመክፈል በየዘርፋቸው በማወዳደር በዓመቱ አፈጻጸማቸው የዓመቱን ደረጃ የሚሰጣቸው ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ መልኩ ደረጃ ተሰጥቷል፡፡

ከቀዳሚዎቹ ወይም የመጀመሪያ ትውልድ ከሚባሉት ከፍተኛ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንደ 2008 ዓ.ም. ሁሉ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2009 ዓ.ም. አፈጻጸሙ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ሲወጣ መቐለና ሀሮማያ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ በዶክተር ደሳለኝ መንገሻ የሚመራው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በማህበረሰብ አቀፍ፣ በምርምርና ማስተማር ዘርፍ ከሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተመራጭ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ይህ ዘንድሮ በተከታታይ የአንደኝነት ሽልማትን እንዲቀዳጅ ያደረገው ድልም በተለይም ከጎንደርና አካባቢዋ ህዝብ ጋር ተሳስሮ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ያገኘው ስኬት ነው፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሰላሙ ዩኒቨርሲቲ በሚል ልዩ ስሙ የሚታወቅ፣ በቱሪዝም፣ ጤና፣ ግብርና ምርምር፣ ህግ፣ ስፖርት እና መሰል ዘርፎች ዙሪያ ጠንካራ ማህበረሰባዊ አቀፍ አገልግሎት በመስጠት ወደ ህዝቡ የቀረበ፤ እንቦጭን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ባለቤት ነኝ ብለው እየሰሩ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም የሆነ ተቋም ነው፡፡ DIRETUBE

 

 

READ  የፊሊፒንሱ ፕሬዘዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ሙሰኛ ባለስልጣናትን ከሄሊኮፕተር ላይ እወረውራለሁ አሉ
Continue Reading

Ethiopia

‹‹በእውኑ መንግስትን ሳያብጠለጥሉ፣ በቻይና እቃ ሳይገለገሉ ለአንድ ቀን መዋል ይቻላልን?››

Published

on

‹‹በእውኑ መንግስትን ሳያብጠለጥሉ፣ በቻይና እቃ ሳይገለገሉ ለአንድ ቀን መዋል ይቻላልን?››

‹‹በእውኑ መንግስትን ሳያብጠለጥሉ፣ በቻይና እቃ ሳይገለገሉ ለአንድ ቀን መዋል ይቻላልን?›› | አሳዬ ደርቤ-በድሬ ቲዩብ

ብዙ ጊዜ መንግስትን የሚያብጠለጥል ጽሑፍ ላለመጻፍ ለራሴ ቃል እገባና ላፕቶፔን እከፍታለሁ፡፡ ይሄን የማደርገው መንግስትን በመፍራት ሳይሆን በመሰላቸት ነው፡፡
እናም ስክሪን ላይ አፍጥጬ የምጽፍበት ርዕስ ሳፈላልግ በከበቡኝ ነገሮች ሁሉ መንግስት እየተከሰተ እንድጽፈው ይወሰውሰኛል፡፡

-ሚስቴ ቡና ይዛልኝ ስትመጣ ከስኒ ማስቀመጫው ላይ የጋንፉር ጨው ፍርካሽ ጎልታ ስታመጣ መንግስት ስኳርን ወክሎ ይከሰታል፡፡
-ላፕቶፔን ቻርጅ ላደርገው ስሞክር ሶኬቱ ውስጥ በኮረንቲ ፈንታ ሃ.ማ.ደ ተሸርኩቶ ይገኛል፡፡
-ባለሱቅ ጎረቤቴ ጋር ደውየ ‹‹የሞባይል ካርድ ላክልኝ›› ስለው ከአምስት ብር ውጭ ካርድ አለመኖሩን ሲያረዳኝ መንግስት የአንድ ነጋዴን ያህል ብርታትና ጥንካሬ አጥቶ በርዕስ መልክ ይገለጻል፡፡
-በመጣልኝ የአምስት ብር ካርድ ፌስቡኬን ከፍቼ ርዕስ ሳፈላልግ…..ከላይ የገለጽኩት አካል አንዱ ሰፈር ላይ- እየገላገለ፣ ሌላው ሰፈር ላይ- ምራቁን ጢቅ አድርጎ ‹‹የማን አባት ገደል ገባ›› እያለ፣ አንዱ ቦታ ላይ- በልማታዊነት፣ ሌላው ቦታ ላይ- በኪራይ ሰብሳቢነት ተሰማርቶ ‹‹ጻፈኝ፣ ጻፈኝ፣ ጻፈኝ›› እያለ ደጅ ይጠናኛል፡፡
-ቃጠሎዬን ለማብረድ ‹‹እስኪ ውሃ ስጡኝ›› ብዬ ስጠይቅ ‹‹ውሃ ከመጣ ሳምንት አለፈው እኮ!›› የሚል መልስ በመክተፊያ ድምጽ ታጅቦ ከጓዳ ይላክልኛል፡፡
በዚህ ጊዜ ነበር ከላይ የገባሁትን ቃል ኪዳን ጥሼ ‹‹በእውኑ በዚህ ዘመን መንግስትን ሳያብጠለጥሉና በቻይና እቃ ሳይገለገሉ ለአንድ ቀን መዋል የሚቻል ነውን?›› የሚል ጥያቄ አንስቼና ይሄንኑ ርዕስ አድርጌ ስለዚህ ‹‹ሰናፍጭ መንግስት›› ልጽፍ ስል ጥያቄዬን የሰማ ቁማርተኛ ጎረቤቴ መዳፉ ላይ በርካታ የመቶ ብር ኖቶች ደርድሮ ‹‹ኧረ ከዚያም በላይ መቆየት ይቻላል!›› እያለ ወደ ቤቴ የገባው፡፡
‹‹እንዴት ተደርጎ?›› ስለው ‹‹ካላመንከኝ እንወራረድ?›› በማለት ስምምነቴን ሳይጠብቅ ወደ ብር ቆጠራ ገባ፡፡
እናም አንድ እንድ ሺህ ብር ካስያዝን በኋላ ከውርርዱ ቀን በፊት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቻይና እጅ የሌለባቸውን እቃዎች የመሰብሰቢያ ጊዜ ተሰጠውና ቅዳሜ ቀን ውርርዱ ጀመረ፡፡
በተባለው ቀን ከአንድ ዳኛ ጓደኛዬ ጋር በማለዳ ወደ ቤቱ ስናመራ የቤቱን በር ክፍቱን አገኘነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ‹‹የቁልፉ ሰረገላ›› በቻይና የተሰራ መሆኑ ነው፡፡
ወደ ሳሎኑ ስንገባ… በባህላዊ መንገድ የተሸመነ ሸማ ለብሶ… ከፊቱ ያስቀመጠውን በቆሎ ጠብሶ ለመብላት ቻይና ሰራሽ የእይታ መነጽሩን ባለማድረጉ የተነሳ እናት አገራችን በቻይና ማሽን አምርታ ስሟን በደማቁ የጻፈችበት ‹ክብሪት› ጠፍቶት እየተንደፋደፈ አገኘነው፡፡ (ክብሪቱን በዳበሳ ለማግኘት በሚጥርበት ወቅት እግረ-መንገዱን የቤቱን ወለል በመዳፉ ማጽዳት ቻለ፡፡)
ከዚያ ቀጥሎ በገል ላይ ክሰል በማቀጣጠል በቆሎውን ጠብሶ ከጨረሰ በኋላ ሳሎኑ ጥግ ላይ ግድግዳ ተደግፎ ከቆመ እንስራ ውሃ የሚቀዳበት ከሸክላ የተሰራ ጽዋ ይዞ ሲነሳ ጓደኛዬ ‹‹ውሃው የተቀዳው ከየት ነው?›› የሚል ጥያቄ አነሳ፡፡
ብርሐን መቋቋም ያቃተውን ዓይኑን በመዳፉ ከልሎ ‹‹ከየት’ስ ቢቀዳ ከቻይና ጋር ምን ያገናኘዋል?›› አለን፡፡
ውሃው ከተቆፈረበት ማሽን አንስቶ እስከሚፈስበት ቧንቧና ቆጣሪ ድረስ የቻይና እጅ እንዳለበት ሲነግረው ‹‹ ሲጀመር ይሄ ሙልፍጥ መንግስት የሰፈራችንን ቧንቧ ከቆረጠው ሳምንት አለፈው አይደለም እንዴ?›› በማለት ውሃውን ከወንዝ እንዳስቀዳው ሊያስረዳን ሞከረ፡፡
ገና በጠዋቱ መንግስትን በማብጠልጠሉ ውርርዱን እንደተሸነፈ ስነግረው ‹‹በቻይና ቁሳቁስ ላልጠቀም እንጂ የመንግስትን ስም ላናነሳ ውል የለኝም›› በማለት ካደኝ፡፡ እናም ሸፍጡን መቀልበስ ባይቻለኝም ውሃውን በተመለከተ ግን በአካባቢያችን ወንዝ ባለመኖሩ ውሃውን ከጠጣ ተሸናፊ እንደሚሆን ዳኛው ሲፈርድበት ጽዋውን በእርግጫ በመጠለዝ ፈርክሶት ተመለሰ፡፡ (የመንግስታችን ጉዳይም እዚሁ ላይ ፍጻሜ አገኘ!)
በማስከተል መልዘዝ የጀመረውን በቆሎ ግጦ ሲጨርስ.. በርኖስ ለብሶ፣ በረባሶ ተጫምቶ ወደ ውጭ ሊወጣ ካለ በኋላ በረባሶው የተሰራበት ‹‹ክርንችት ሚስማር›› የቻይና ግብዓት መሆኑ ትዝ ሲለው ‹‹ለነገሩ ጫማው የአገሬ ምርት ቢሆንስ በየትኛው መንገድ ላይ እሄዳለሁ›› በማለት ጫማውን ወርውሮ ከአጠገቡ ካገኘው ባርጩማ ላይ ‹አባ-ጅፋርን› መስሎ ተቀመጠ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ደግሞ ልክ እንደ ቴሌቪዥኑ ሁላ ቻይና ሰራሽ ስልኩን በማጥፋቱ የተነሳ ልታገኘው ያልቻለች ገርል ፍሬንዱ (ሮዚ) ከደጅ ጀምራ ስሙን እየተጣራች ስትገባ በአካሏ ላይ ካሉት መዋቢያዎች ውስጥ አንድም የቻይና ምርት ያልሆነ አይታይም ነበር፡፡ ጥርሷ ላይ ያስገጠመችው ብሬስ፣ ጸጉሯን ያበጠረችበት ማበጠሪያ፣ የተቀባችው ቅባትና ቀለም፣ የታጠቀችው ሱሪ ከእነ ቀበቶው፣ ሁሉም የቻይና የእጅ-ስራ ነበሩ፡፡
ልክ እንደገባች እጮኛዋ ሸማ ለብሶና የድንጋይ ዘመንን ወደ ኋላ መልሶ በመመልከቷ የተነሳ ‹‹ምን እየተካሄደ ነው?›› ከሚል ጥያቄ ጋር ልትስመው ወደ ጉንጩ ስትጠጋ ‹‹በህግ አምላክ አትጠጊኝ›› በማለት ተፈናጥሮ በሚነሳበት ወቅት በሸማ የተጋረደው እርቃኑ በከፊል ተጋለጠ፡፡ (ፓንቱን ጨምሮ ያሉት አልባሳቶች የቻይና በመሆናቸው አውልቆ ጥሏቸዋል፡፡)
ለሮዚ ስለ ውርርዱ እየነገርናት በሳቅ ስትደክም ቆየችና በስተመጨረሻ ተመልሳ ከመሄዷ በፊት ‹‹ባለፈው የሰጠሁህን መጽሐፍ አምጣልኝማ!›› ስትለው ሸማውን እየገተተ ወደ መኝታ ቤቱ አመራ፡፡
እናም የመኝታ ቤቱን አምፖል በማብራት እቃዎችን ሲያተራምስ ቆይቶ ‹‹ታላቁ-ተቃርኖ›› የሚል መጽሐፍ ይዞ ተመለሰ፡፡
እግረ-መንገዱንም በቻይና ማብሪያ ማጥፊያ፣ የቻይናን አምፖል በማብራት ራሱን ተቃርኖ አረፈው፡፡
‹‹ቢንጎ!›› ብዬ ስጮህ ቁማርተኛው ስህተቱ ገብቶት ‹‹አይ ሄዋን! እግዜር ይይልሽ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?›› በማለት ራሱን ይዞ ተቀመጠ፡፡
እናም ‹‹ቻይና የለሌችበት ምርት፣ መንግስት የማያመጣው ጉድለት አይኖርም›› አላልኩህም ስለው ‹‹ሴት የሌለችበት ስህተት የሚል ሃረግ ጨምርበት›› ብሎኝ ልብሱን ሊለብስ ወደ መኝታ ቤቱ አመራ፡፡

READ  ግሸን መድሀኒት ቤት አበረታች መድኃኒት አስመልክቶ ዘጋርዲያን የተባለው ጋዜጣ የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ላወጣው ዘገባ ምላሽ ሰጠ

 

 

 

 

Continue Reading

Trending

news.et Mobile App!

It's Faster!

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close