Connect with us

Health

የእንቅልፍ ልብ ጉዞ (ስሊፕ ዎኪንግ) ምንድነው ? መንስኤው እና መፍትሄዎቹስ ?

Binyam G-Kirstos

Published

on

የእንቅልፍ ልብ ጉዞ (ስሊፒ ዎኪንግ) ምንድነው ?

የእንቅልፍ ልብ ጉዞ (ስሊፕ ዎኪንግ) ምንድነው ? መንስኤው እና ምፍትሄዎቹን ? – ሳይንትፊክ መጠሪያው ፓራዞሚንያ ይባላል ይህ በእንቅልፍ ላይ እያሉ በእውን እንዳለ ሰው መንቀሳቀስ አሊያም የተለያዩ ተግባራትን የማከናወን ተግባርን፡፡

በርግጥ ይህ ችግር እንደ በሽታ ባይቆጠርም የበሽታን ያህል ግን ጉዳት ላይ ሊጥል ይችላል፡፡ የኢትዮፒካ ሊንክ የሬድዮ ፕሮግራም ስለዚህ ጉዳይ መንስኤ እና ስለ መፍትሄ ሃሳቦቹ ያቀረበውን ፕሮግራም በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡

ፓራዞሚንያ ወይም የእንቅልፍ ልብ ጉዞ መንስኤ ይህ ነው ተብሎ በውል የተረጋገጠ ጉዳይ የለም፡፡ የህክምና ባለሞያዎችም የተለያዩ መላምቶችን ከመስጠት ባለፈ እርግጥ ያለ መነሻው እና መንስኤው ላይ አልደረሱበትም፡፡

ይህ ችግር ከአስራ ሶስተ እስከ አስራ ስምንት የእድሜ ክልል ላይ በሚገኙ ህጻናት ላይ በሰፊው ይከሰታል፡፡ ለመጀመሪያ ግዜም በኪነጥበብ ስራ ላይ የዚህ ችግር ያለበት ገጸባህሪ የታየው በሼክስፒር ግዜ እንደሆነ እና ገጸባህሪዋ በእንቅልፍ ልቧ በምታደርገው እንቅስቃሴ ከኬሎች ሰዎች ጋር ተባበራ አባቷን እንደገደለችው የሚያሳይ ነው፡፡ ከዚያም ግዜ በኋላ ይህ የእንቅልፍ ልብ ጉዞ በበርካቶች እየታወቀ መጥቷል፡፡

አራት አይነት የእንቅልፍ ደረጃዎች ሲኖሩ ይህ ችግር የሚከሰተው በሶተኛው የእንቅልፍ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ነገር ግን እድሚያችን እየጨመረ ሲመጣ ችግሩ እየቀነሰ ይመጣል፡፡

እነዚህ የእንቅልፍ ደረጃዎች ላይ ለመድረስ ከ ሰላሳ ስስከ ዘጠና ደቂቃ የሚወስድ ሲሆን በችግሩ የሚጠቃ ሰው በእንቅልፍ ልቡ ልክ በእውን እንዳለ ሰው የተለያዩ ድርጊቶችን የሚያከናውነው ከ አስር እስከ ሰላሳ ደቂቃዎች ድረስ ነው፡፡

የእንቅልፍ ልብ ጉዞ በሸለብታ ወቅት የሚከሰት አይደለም፡፡ ይህ የእንቅልፍ ግዜ እቅልፍ ከተጀመረ ከ አስር እስከ ሰላሳ ደቂቃ ያለውን የእንቅልፍ ግዜ የሚያመለክት ነው፡፡

ይህ ችግር እንዴት ይከሰታል ? ለሚለው የተለያዩ መላ ምቶች የሚሰጡ ሲሆን ችግሩ በመንታ ልጆች ላይ የመከሰት እድሉ ይጨምራል፡፡

በዘር ሊተላለፍ ይችላል የሚለው ሌላ መላምት ሲሆን የእንቅልፍ እጦት ፣ የተመሰቃቀለ እንቅልፍ ፣ ራስ ምታት ፣ ጭንቀት ፣ አልኮል በብዛት መጠጣት ፣ ለእንቅልፍ እና ለአእምሮ በሽታ የምንወስዳቸው መድሃኒቶች  ፣ ሃይል ለማግኘት የሚወሰዱ መድሃኒቶች እና ለአለርጂ የሚወሰዱ መድሃቶኒች  ለዚህ ችግር ሊያጋልጡ እንደሚችሉ ይገለጻል፡፡

በእንቅልፍ ልቡ እየተጓዘ ያለን ሰው እንዴት መለየት ይቻላል ? ለሚለውም በእንቅልፍ ልቡ ያለ ሰው ከወትሮ በተለየ የመፍዘዝ እና የመደንዘዝ ስሜት ይታይበታል ፣ በሚያወራበት ወቅትም የመደንዘዝ እና የማፍጠጥ ብሎም ከፍተኛ ላብ የሚታይበት ሲሆን ህጻናት ደግሞ ለወትሮ ከቤተሰብ ጋር ሲሆኑ የማያሳዩትን ‹‹የውጭ/ የትምህርትቤት›› ባህሪያቸውን በዚህ በእንቅልፍ ልብ ጉዞ ወቅት ያሳያሉ፡፡

በችግሩ የሚጠቁ ሰዎች በዚህ ምክንያት የሚደርስባቸን አደጋ እና ችግር ለማስወገድ አልኮል አለመጠቀም ፣ ያለ አልጋ ፍራሽ ላይ መተኛት (ከአልጋ ወድቆ እንዳይጎዱ)፣ ከመተኛት በፊት በር እና መስኮቶችን መቆለፍ እና ቁልፎቹንም ውሃ ውስጥ መክተት ይህ በእንቅልፍ ልብ ጉዞ ወቅት ቁልፎቹን ለማውጣት እጅ ውሃ ውስጥ በሚገባበት ወቅት ከእንቅልፍ ልብ ጉዞ ለመንቃት ያስችላል፡፡

የእንቅልፍ ሰዓትን ወጥ ማድረግ ፣ መመሰጥን መለማመድ ፣ የሚያፍታቱ ስፖርቶችን ማዘውተር ፣ ንጹህ የሆነ መኝታ ቤት እንዲኖር ማድረግ ችግሩ ላለባቸው ሰዎች መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጭንቀትን እና ውጥረትንም ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close