በየመን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አስከፊ ግዜ እያሳለፉነው ተባለ

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ቢሮ (አይኦኤም) ባሳለፍነው ዓመት በስደት ጉዞ 7189 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉን እና ለስደት ወጥተው ደብዛቸው የጠፉትን ሰዎች መዝግቧል ሲል በየመን ኢትዮጵያዊ ስደተኛን በማነጋገር ዘገባ የሰራው ቪኦኤ ዘገባውን ይጀምራል፡፡

በዚሁ ዓመትም በአማካኝ በቀኑ 20 ስደተኞች ህይወታቸው ማፉን የስደተኞቹ ቢሮ ሪፖርት እንደሚያሳይም ተጠቅሷል፡፡

ይህ ቁጥር ካለፈው 2015 ጋር ሲነጻጸርም ቁጥሩ ክፍተኛ ነውም ተብሏል ፡፡

እ.ኤ.አ በ2014 ለስደት ወጥተው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 5667 የነበረ መሆኑን እንዲሁም በ2015 ደግሞ በተመሳሳይ ለህልፈት የተዳረጉ ስደተኞች ቁጥር 5740 እንደነበር በማነጻጸሪያነት ቀርቧል፡፡

ከሰሜናዊ እና ከምስራቅ አፍሪካ በተለይም ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከሶማሊያ እና ከጅቡቲ የሚሰደዱ ስደተኞች ሞት ቁጥርም ከላይ ከተጠቀሰው የሞት መጠን የላቀውን ድርሻ ይይዛል ይላል ዘገባው፡፡

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመትም በግምት 700 የሚሆኑ ስደተኞች ከእነዚህ ሀገራት ህይወታቸው አልፏል  ተብሏል፡፡

ስሙ እንዲጠቀስ አልፈለገም የተባለ አንዲ ኢትዮጵያዊ ስደተኛን መስታወት አራጋው በስልክ ስለ ስደት ሂወቱ የተለያየ ጥያቄ አቅርባለት ነበር፡፡

አብዛኛውን ጉዞውን በእግር እንዲሁም ሲገኝም በተሸከርካሪ በመጓዝ የመን መድረሱንም ይህ ስደተኛ ኢትዮጵያዊ  ይናገራል፡፡

ስሜ አይጠቀስ ብሏል የተባለው ወጣት ‹‹አብዛኞቻችን እዚህ የምንገኘው ስደተኞች ኑሮ ቸግሮን ሳይሆን ሀገራችን ላይ እንደዜጋ መኖር አቅቶን ነው ከሀገራቸን የተሰደድነው›› ሲል ተደምጧል፡፡

ከኢትዮጵያ የወጣው እ.ኤ.አ በ2014 መሆኑን እና የጉዞው ሂደትም ከኢትዮጵያ ተነስቶ ሱማሌ ለመድረስ በርካታ ችግሮችን ተጋፍጦ ከሶማሌ በጀልባ የመን መግባቱን ተናግሯል፡፡

የመን ከገባ በኋላ የገጠመው ችግር ‹‹ተወርቶ አያልቅም የሚለው ወጣቱ›› መንገድ ላይ ሱማሌዎች እየደበደቡን ሴቶች እየተደፈሩ የሚበላ ነገር ሳይኖር ሰላሳ ሰዓት በሚፈጅ የባህር ጉዞ የመን ግተናል ብሏል፡፡

READ  ከተለያዩ አካባቢዎች ለመጡ ሶስት መቶ አካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ እግር ተከላ እየተደረገ ይገኛል

የመን ከገቡ በኋላም የረዳቸው ሰው አለመኖሩንእንደውም በእዛው በየመን ጦርነት በመኖሩ በፍርሃት እየኖርን ነው ሲል ተደምጧል፡፡

ወጣቱ ስደተኛ ከኢትዮጵያ ከእስር ቤት አምልጬ ራሴን ለማዳን ነው የወጣቡት ያጣሁት ወይም ኑሮ የቸገረኝ ሰው አይደለሁም ፤ በወቅቱ ከኢትዮጵያ ስወጣም ወዴት እንደምሄድም አላውቅም ነበር ያለ ሲሆን በርካቶቹ አብረውት የተሰደዱት ኢትዮያዊያን ኦሮምኛ ተናጋሪ እንደሆኑ ገልጿል፡፡ ሴቶች እንደሚበዙም ተናግሯል፡፡

በየመን ‹‹በሞት እና በህይወት መካከል ነው የምንገኘው›› የሚለው ወጣቱ የስደተኞች ተቋምም የሚረዳን ነገር የለም ፤ እየተደበቅን ነው ህይወታችንን ለማቆየት የምንጥረው ብሏል፡፡

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ቢሮ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት ሜዲትራንያንን ለማቋጥ ከሞከሩ ስደተኞች መካከል የ4812 ህይወት ያለፈ መሆኑን ማስታወቁም በዘገባው ተጠቁሟል፡፡

የቪኦኤን ሌሎች ዘገባዎችንም መከታተል ይችላሉ፡፡

NO COMMENTS