Connect with us

አማርኛ

ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ያሉ መንገዶች የስጋት ቀጠና ሆነዋል

Elias Tesfaye

Published

on

የስጋት ቀጠና

ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ስወጡ መንገዶች የስጋት ቀጠና ሆነዋል፡፡ በጌዴኦ ዞን የተፈጠረው ብጥብጥ በዜጎች ላይ አለመረጋጋትን ፈጥሯል

የኢሬቻ ዕለት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከዕለቱ ዕለት ጀምሮ የተነሳው ብጥብጥ አሁን ድረስ አልተረጋጋም፡፡ በርካታ መኪናዎች ተቃጥለዋል፡፡ ጎዳናዎች ዝግ ሆነዋል፡፡ የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ተገትቷል፡፡

ከአዲስ አበባ ጅማ እና ከአለም ገና አዋሽ እንዲሁም ከሞጆ እስከ ጥቁር ውሃ እና አጄ፣ ከቡራዮ እስከ አምቦ፣ ከሱሉልታ እስከ ጎሃ ጽዮን ያለው መንገድ ለየብስ ተሸከርካሪዎች አሳር ሆኗል፡፡

ከጫካ ውስጥ ተሸሽገው ሆ ብለው በመውጣት ከባድ መኪናዎችን ዶግ አመድ የሚያደርጉ ወጣቶች እና መንገድ የሚዘጉ ሴቶችና ህጻናት አመጹን መራር አድርገውታል፡፡ መኪኖች ከየት አቅጣጫ እንደተወረወረ በማይታወቅ ድንጋይ መስታወታቸው ዶግ አመድ ይሆናል፡፡ ሪፖርተሮቻችን በዚህ አስቸጋሪ በሚባሉ የብጥብጥ መስመሮች ተንቀሳቅሰው እንደአረጋገጡት የጸጥታ ሃይሎች መንገዶቹን ሙሉ ለሙሉ ለደህንነት ምቹ አላደረጓቸውም፡፡

በተያያዘ ዜና በጌዴኦ ዞን የተነሳው ብጥብጥ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ገልጸዋል፡፡ በዲላ እና ይርጋጨፌ የተነሳው ተቃውሞ እስከአሁን ዓላማው በግልጽ አልታወቀም፡፡ መስጂዶችና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት የጥቃት ቀጠና ሆነዋል፡፡ አንዳንዶች በአማራ፣ በጉራጌና በስልጤ ላይ ያነጣጠረ የዘር ጥቃት እና ዞናችንን ለቃችሁ ውጡልን ግፊት እንደአለ እየገለጹ ነው፡፡ የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ መኖሪያ ቤት ተቃጥሏል፡፡ ብጥብጡን ተከትሎ የተፈጠረው የደህንነት ስጋት እንደቀጠለ ነው፡፡

Trending

By continuing to use the site, you agree to the use of cookies. more information

The cookie settings on this website are set to "allow cookies" to give you the best browsing experience possible. If you continue to use this website without changing your cookie settings or you click "Accept" below then you are consenting to this.

Close