Connect with us

የዳዳብ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ገለጹ

Afar Region
Photo: Afar Region

ማህበራዊ

የዳዳብ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚፈልጉ ገለጹ

Nemo enim ipsam voluptatem quia voluptas sit aspernatur aut odit aut fugit.

ስደተኞቹ ከኬንያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት ተወካዮች እንዲሁም በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ዳዳብ ውስጥ ባደረጉት ውይይት ወደ ሀገራቸው በመመለስ እንደሌሎች ወገኖቻቸው ህይወታቸውን መምራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

እስከ 30 ዓመት ለሚሆን ጊዜ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የቆዩት 4,500 ያህል ስደተኞች መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ባለስልጣን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያረግላቸው ጠይቀዋል። አብዛኛዎቹ ስደተኞች ከኦሮሚያ ሱማሌ እና ጋምቤላ ክልሎች የመጡ ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ምክትል ኃላፊ ዎልፑርጋ ኢንግፕሬክት በበኩላቸው ስደተኞቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን የፋይናንስና ሌሎች ድጋፎች እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

አምባሳደር መለስ በበኩላቸው በተመሳሳይ መንግስትም ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለማስገባት የሚቻለውን እነደሚያደርግ በመግለጽ ከስደተኞቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከአለማችን ትልቁ የስደተኞች ካምፕ የሆነው ዳዳብ በአሁኑ ወቅት 200,000 ያህል ስደተኞች ያሉት ሲሆን አብዛኞቹ የሶማሊያ ስደተኞች ናቸው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
2 Comments

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top