ሴቶችን በማብቃት ላይ የሚሰራው የ የኛ ፕሮጀክት የታብሎይድ ጋዜጦችና የወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ሰለባ ሆኗል ተባለ

0
484
ሴቶችን በማብቃት ላይ የሚሰራው የ የኛ ፕሮጀክት የታብሎይድ ጋዜጦችና የወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ሰለባ ሆኗል ተባለ
ሰሞኑን የብሪታኒያ አለም አቀፍ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ በሴቶች ልማት ላይ የሚሰራውን የ የኛ ፕሮጀክትን መደገፍ ማቆሙን አስታውቋል፡፡

ሰሞኑን የብሪታኒያ አለም አቀፍ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ በሴቶች ልማት ላይ የሚሰራውን የ የኛ ፕሮጀክትን መደገፍ ማቆሙን አስታውቋል፡፡ የኛ የሚል ስያሜ የተሰጠውና በኢትዮጵያ ሴቶችን በማብቃት ላይ ለሚሰራ ፕሮጀክት ሲሰጥ የቆየው ይህ ገንዘብ በብሪታኒያ ምክር ቤት ውሳኔ እንዲቆም መደረጉ አለም አቀፍ መነጋገሪያ ፈጥሮ ነው የሰነበተው፡፡

አምስት እንስቶችን ያቀፈው የኛ በሙዚቃና በድራማ ስራዎች በሴቶች ላይ ስለሚደርሱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም ስለጾታ እኩልነት የማስተማርና የመቀስቀስ ስራዎች እንደሚሰራ ይነገራል፡፡

እንደ ዴይሊ ሜል ያሉ የብሪታኒያ መገናኛ ብዙሀን ፕሮጀክቱ ስኬታማ አይደለም በማለት የሀገሪቱ መንግስት ድጋፉን እንዲያቋርጥ መወትወት ከጀመሩ ከራርመዋል፡፡ ይህንኑ ሀሳብ ይዘው በሀገሪቱ ፓርላማ ጉዳዩን ያቀረቡ ፖለቲከኞችም ውትወታቸው የኋላ ኋላ ሰሚ አግኝቶ እርዳታው እንዲቋረጥ አስወስነዋል፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ለቪኦኤ አማርኛ ዝግጅት ምላሽ የሰጡት የየኛ ፕሮጀክት ሀላፊ ከሆኑት አንዷ ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ ውሳኔው የወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች እርምጃ ነው ሲሉ ነበር የተናገሩት፡፡

አሁን ላይ በብሪታኒያ ቀኝ ዘመም የሆኑ እርዳታ መስጠትንና ስደተኞችን መቀበል የሚጠሉ ፖለቲከኞች ተጽእኖአቸው ከፍ እያለ መጥቷል ያሉት ወ/ሮ ሰሎሜ ውሳኔው የዚህ ተጽእኖ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር የሚመሳሰል ዜና ያስነበበው ኳርትዝ የወሬ ምንጭ በበኩሉ ሴቶችን ለማብቃት የሚሰራው የኛ ፕሮጀክት እንደ ዴይሊ ሜል ያሉ ታብሎይዶችና የወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ሰለባ ሆነ በማለት ጉዳዩን ዘግቦታል፡፡

Ethiopia’s “Spice Girls” are the first victims of a tabloid campaign for the UK to cut foreign aid
The British government has stopped funding an aid program aimed at empowering Ethiopian girls after a concerted campaign by tabloid newspaper and Conservative party politicians to cut foreign aid spending.

READ  ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጡ

The UK’s Department for International Development announced on Jan. 6 it was pulling funding to Girl Effect, a non-profit that uses pop culture and mobile technology to empower young girls that it has supported since 2010. Conservatives took issue with the organization’s main outreach program: Yegna, a band of five young Ethiopian women who use their music, talk show and weekly radio drama to talk about early marriage, gender-based violence, education and self-worth.

“Empowering women and girls around the world remains a priority, but we judge there are more effective ways to invest UK aid and to deliver even better results for the world’s poorest and value for taxpayers’ money,” the department said in a statement on Jan. 6.
UK foreign aid spending on groups like Yegna have been the target of criticism by the Conservative Party MPs and the Daily Mail tabloid for some time.

Read More:https://qz.com

NO COMMENTS