ኢትዮጵያ በፈቱላ ጉለን ድርጅት የተመሰረቱ ትምህርተ ቤቶችን ለቱርክ መንግስት ለማስተላለፍ መስማማቷ ተዘገበ

0
2267
ኢትዮጵያ በፈቱላ ጉለን ድርጅት የተመሰረቱ ትምህርተ ቤቶችን ለቱርክ መንግስት
በቱርክ በቅርቡ የከሸፈ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ ከዚህ አደጋ የተረፈው የሬሲብ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስትም በርካታ ሀይል የተቀላቀለባቸውና የሰብአዊ መብት ክሶች የቀረበባቸው እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል፡፡

በቱርክ በቅርቡ የከሸፈ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ ከዚህ አደጋ የተረፈው የሬሲብ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስትም በርካታ ሀይል የተቀላቀለባቸውና የሰብአዊ መብት ክሶች የቀረበባቸው እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወቃል፡፡

ከዚህ እርምጃ ጎን ለጎንም የቱርክ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን አቀነባባረዋል ባላቸው በሲአይኤ ጥበቃ ስር በአሜሪካ ተጠልለዋል በሚባሉት ፈቱላ ጉለን ላይ ጣቱን መቀሰሩ ይታወቃል፡፡ ሰውየውን አምርሮ የሚጠላው የኤርዶጋን መንግስት ከፈቱላ ጉለን ጋር የተገናኙ

ተቋማትን በቱርክና በመላው አለም ከመዝጋት በተጨማሪም በእርሳቸው ይንቀሳቀሳሉ የሚባሉ ንብረቶችንም መያዙ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
ይህንኑ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ በርካታ የቱርክ አጋር ነን የሚሉ መንግስታት የኤርዶጋን መንግስትን ቁጣ ለማብረድ በሚል በፈቱላ ጉለን የተቋቋሙ ድርጅቶችንና ትምህርት ቤቶችን ዘግተዋል፡፡

በኢትዮጵያም ስድስት ተማሪ ቤቶች በፈቱላ ጉለን እርዳታ መቋቋማቸው ይነገራል፡፡ የቱርኩ አናዶሉ የዜና አውታር የእነዚህ ተማሪ ቤቶች አስተዳደር ለቱርክ መቼ ነው ተላልፎ የሚሰጠው የሚል ጥያቄ ሰሞኑን ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ማንሳቱን ዘግቧል፡፡

ይህን በሚመለከት ሁለቱ ሀገራት ጉዳዩን በህግ አግባብ እየሄዱበት መሆኑን ለዜና ምንጩ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ትምህርት ቤቶቹ በህጋዊ መንገድ ለቱርክ ተላልፈው ይሰጣሉ ማለታቸውን ዘግቧል፡፡

በቅርቡ የቱርክ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ኒሀት ዜይቤኪ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ጉዳዩን እንዳነሱላቸው የተናገሩት አቶ ሀይለማሪያም በነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ስላሉ ጉዳዩ በፍጥነት ለመካሄድ እንደዘገየ አስረድተዋል፡፡ በተማሪ ቤቶቹ የሚማሩ ተማሪዎች ለችግር በማይዳረጉበት መንገድ ጉዳዩ በህጋዊ መንገድ ተገባዶ ለቱርኮች ይተላለፋል ሲሉም ስለነዚህ ተቋማት ይዞታ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ ለብሄር ብሄረሰቦች በአል ዘገባ ሀረር የተገኘው የአናዶሉ ዜና አውታር ልኡክ ለጋዜጠኞች ማደሪያነት የተሰናዳው ማረፊያ በፈቱላ ጉለን የተሰራ ተማሪ ቤት ነው በሚል ተቃውሞ ማቅረቡ በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ሲዘገብ መሰንበቱ አይዘነጋም፡፡aa

READ  ለፊደል ካስትሮ የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ

NO COMMENTS