ቤተ እስራኤላዊያን ደም መለገስ የሚያስችላቸውን ህግ የእስራኤል መንግስት አረቀቀ

0
605
ቤተ እስራኤላዊያን ደም መለገስ የሚያስችላቸውን ህግ የእስራኤል መንግስት አረቀቀ
እንደአውሮፓዊያኑ በ 1977 በእስራኤል መንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የወጣው ህግ ከኢትዮጵያ ወደሀገሪቱ የገቡ ቤተ እስራኤላዊያን ለሀገሪቱ ደም ባንክ ደም መለገስ አይችሉም ሲል ይከለክላል፡፡

እንደአውሮፓዊያኑ በ 1977 በእስራኤል መንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የወጣው ህግ ከኢትዮጵያ ወደሀገሪቱ የገቡ ቤተ እስራኤላዊያን ለሀገሪቱ ደም ባንክ ደም መለገስ አይችሉም ሲል ይከለክላል፡፡

የእስራኤል መንግስት ይህን ያደረኩት የሀገሬን ህዝቦች ከኤች አይቪና ከሌሎች በሽታዎች ተጋላጭነት ለመታደግ ነው ሲል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ህግ ቤተ እስራኤላዊያኑ በፖሊሲ የተደገፈ መድሎና መገለል ሲሉ እስከ ቅርብ ጊዜ ሲታገሉት ቆይተዋል የሚለወው ሀሬትዝ የዜና ምንጭ አሁን ላይ ህጉ ሙሉ ለሙሉ ሊቀየር ስለመሆኑ ዘግቧል፡፡

ሀሬትዝ እንዳለው ከሆነ የእስራኤል የጤና ሚኒስቴር ቤተ እስራኤላዊያን ያለገደብ ደም መለገስ የሚያስችል አዲስ ህግ አርቅቋል፡፡ ይህ ህግ ደግሞ በመጪው ሀምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል፡፡

አዲሱ ህግ ቤተ እስራኤላዊያን ብቻ ሳይሆን ግበረ ሰዶማዊያንና እድሜያቸው ከ 65 አመት በላይ የሆኑ አረጋዊያንንም ደም የመለገስ መብት ያጎናጽፋቸዋል ነው የተባለው፡፡ israelnationalnews

READ  Esmeralda Farms Closes Down following Attack

NO COMMENTS