ጫት ባለፉት አምስት ወራት 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል ተባለ

0
1355

ጫት ባለፉት አምስት ወራት 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል ተባለ – ሸገር 10.1 ሬድዮ ጣቢያ እንደዘገበው ባለፉት አምስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች አንድ ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታስቦ የተገኘው አንድ ነጥብ ዜሮ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው ተብሏል፡፡

ይህም በመቶኛ ሲሰላ ከእቅዱ የተሳካው ስልሳ ነጥብ ሶስት አራት በመቶ ብቻ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም አርባ ዘጠን ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አለው ይላል ዘገባው ፡፡

የተሳካው ስልሳ ነጥብ ሶስት አራት በመቶ ብቻ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም አርባ ዘጠን ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አለው ይላል ዘገባው ፡፡

በንግድ ሚኒስቴር ተወካይ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሽመልስ አረጋን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው ለገቢው መቀነስ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ  ሀገራት የምትልካቸው ምርቶች በጥራት ረገድ ተወዳዳሪ መሆን አለመቻላቸው በዋነኝነት ይጠቀሳል፡፡

የዓለም ገበያ መቀዛቀዙም ሌላው ምክንያት ነው ተቧል፡፡

ከተገኘው ገቢ ውስጥ አንድ መቶ ሺህ ቶን የቅባት እህል ተልኮ አንድ መቶ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል፡፡

በሌላ በኩል ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች መካከል ጫት ጥሩ የሚባል ገቢ ያስገኘ ሲሆን ባለፉት አምስት ወራት ጫት አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ዶለር አስገኝቷል ተብሏል፡፡

ቅመማ ቅመም ባህር ዛፍ እና የተቆላ ቡና ከመቶ ፐርሰንት በላይ ገቢ ያስገኙ ናቸው፡፡

የጥራጥሬ ሰብሎች ፤ የተፈጥሮ ሙጫ ፤ እጣን ፤ ጫት እና የቅባት እህሎች ከታቀደላቸው የገቢ መጠን ከ ሰባ አምስት እስከ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ያሳኩ ምርቶች ሲሆኑ የኮንስትራክሽን እና የኬሚካል ግብአቶች ፤ ሞላሰስ ታንታለም እና ሌሎች ማእድናት ፤ ማር እና የቁም እንስሳት ይገኝባቸዋል ከተባለው ገቢ ከሃምሳ በመቶ በታች ቀንሰዋል ተብሏል፡፡

READ  ከ17 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬትን በህገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች እንዲሰጥ ያደረጉ የጫንጮ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

NO COMMENTS