ጎ – ገበያ (GoGebeya) የተባለ ነጻ የኢትዮጵያ የኦንላይን ግብይት አፕሊኬሽን ይፋ ሆኗል – News.et

0
494

ጎ – ገበያ የተባለ ነጻ የኦንላይን ግብይት አፕሊኬሽን ይፋ ሆኗል – የታዲያስ አዲስ አዘጋጆች እንዳወሩት ከሆነ ነጋዴውን እና ገዢውን በፈጣን እና በታማኝነት ለማገናኘት የሚያስችል ከክፍያ ነጻ የሆነ የሞባይል አፕሊኬሽን ይፋ ሆኗል፡፡

የአፕሊኬሽኑ ፈጣሪ አቶ ቢንያም ነገሱ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ጋር በስልክ ባደረገው ቆይታ አፕሊኬሽኑ ገዢን እና ሻጭን በቀላሉ ለማገናኘት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን አፕሊኬሽኑ በገዥ እና በሻጭ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያለግል ነው ብሏል፡፡

ይህ አፕሊኬሽን ነጋዴዎችን ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችንም ማእከል ያደረገ ሲሆን ማንኛውም ሰው ያለውን ያገለገለ አሊያም አዲስ እቃ መሸጥ ቢፈልግ አፕሊኬሽኑን በቀላሉ ተጠቅሞ ከገዢ ጋር መገናኘት እንደሚቻልም ተጠቁሟል፡፡

አፕሊኬሽኑ የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ያለው በመሆኑ ገዢ በአቅራቢያው ያለውን ሻጭ እንዲገኝ ያስችለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አፕሊኬሽኑ ለተመሳይ እቃዎች የቀረቡ የተለያዩ ዋጋዎችን የሚያቀርብ በመሆኑ አወዳድሮ ለመግዛትም ይቻላላ ተብሏል፡፡

ታማኝነትን በተመለከተ ማንኛውም ገዢ ለመግዛት የሚፈልገውን እቃ ሻጭን በቻት ካገኘ እና ከተስማማ በኋላ በስልክ ተነጋግረው በአካል ግብይት የሚፈጸም በመሆኑ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የሚደርስ ማጭበርበር አይታሰብም ተብሏል፡፡

ምናልባት የሌለውን እቃ አለኝ ብሎ የሚወጣም ካለ ተጠቃሚው ሬት (የታማኝነት መለኪያ) ስለተዘጋጀለት እና ገዢው ይህን የታማኝነት መለኪያ ስለሚሰጠው ለሌለው ገዢ ጥቆማ ሆኖ ያገለግላል፡፡

አፕሊኬኑሽ ከገዢውም ሆነ ከሻጭ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይጠይቅ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የዚህ አላማ አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ወደፊት ከማስታወቂያ ገቢ ለማግኘት በመሆኑ አገልግሎቱን ማስተዋወቅ ቅድሚያ ተሰጥቶታል ብሏል የአፕሊኬሽኑ ፈጣሪ አቶ ቢንያም ነገሱ፡፡

READ  በታላቅ ወንድማቸው የተደፈሩት እህትና ወንድም አሳዛኝ ታሪክ ….

NO COMMENTS