ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ዶ/ር መረራ ከአሸባሪዎች ጋር አሲረዋል ሲሉ ተናገሩ

0
4109
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ዶ/ር መረራ ከአሸባሪዎች
ዶ/ር መረራን መንግስታቸው ከእስር እንደማይለቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል

ዶ/ር መረራን መንግስታቸው ከእስር እንደማይለቃቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል

ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በእስር ላይ የሚገኙትን አንጋፋ የተቃውሞ ፖለቲካ ሰው ዶ/ር መረራ ጉዲናን በተመለከተ ከመገናኛ ብዙሀን ጥያቄ እንደቀረበላቸው ተነግሯል፡፡ በዚሁ ጊዜ ዶክተር መራራ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር በማሴር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስታቸው ታሳሪውን የሚፈታበት አንዳችም ምክንያት እንደማይኖር መግለጻቸውን ሱዳን ትሪብዩን ዘግቧል፡፡

ቪኦኤ የዜና ምንጭም ይህንኑ ጉዳይ በሚመለከት ባወጣው ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክተር መረራ እስር በህግ አግባብ የሚታይ እንጂ ለፖለቲካ ሲባል የተደረገ አለመሆኑን መናገራቸውን ገልጿል፡፡

ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው ማለታቸው የተነገረው አቶ ሀይለማሪያም ዶ/ር መረራ የታሰሩትም ይህንኑ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ተጋብዘው ብራሰልስ በተገኙበት ወቅት መንግስት በአሸባሪነት ከፈረጃቸው ከግንቦት 7 መሪ ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር በመገናኘታቸው ወደሀገር ቤት ሲመለሱ መንግስት በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ይታወሳል፡፡

ሁለት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት ዶ/ር መረራ ጠበቆቻቸው ግን እስከአሁን ይህ ነው የሚባል ክስ እንዳልተመሰረተባቸው በቅርቡ ገልጸዋል፡፡
sudantribune

READ  Pan-African Fashion Show in Ethiopia

NO COMMENTS