የጀርመኑ ግሪን ፓርቲ መንግስት የዜጎችን የወሲብ ወጪ መሸፈን ይገባዋል ሲል ጥያቄ አቀረበ

0
2810
የጀርመኑ ግሪን ፓርቲ መንግስት የዜጎችን የወሲብ ወጪ መሸፈን ይገባዋል ሲል ጥያቄ አቀረበ
በአንዳንድ ሀገራት መንግስታት የተለያዩ የዜግነት ጥቅማ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፡፡ ትምህርት፣ ውሀ፣ የኢነርጂ ወይም መጠለያ አቅርቦት በነጻ ለዜጎቻቸው የሚደጉሙ መንግስታት በርካታ ናቸው፡፡ ለዜጎቻቸው የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉም አሉ፡፡ ጀርመን ደግሞ አሁን አዲስ ድጎማ ይዛ ብቅ ማለቷ ነው የተነገረው፡፡ ዴይሊ ሜል እንደዘገበው ከሆነ የሀገሪቱ ግሪን ፓርቲ መንግስት የዜጎችን የወሲብ ወጪ መሸፈን አለበት የሚል እቅድ አቅርቧል ብሏል፡፡

በአንዳንድ ሀገራት መንግስታት የተለያዩ የዜግነት ጥቅማ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፡፡ ትምህርት፣ ውሀ፣ የኢነርጂ ወይም መጠለያ አቅርቦት በነጻ ለዜጎቻቸው የሚደጉሙ መንግስታት በርካታ ናቸው፡፡

ለዜጎቻቸው የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉም አሉ፡፡ ጀርመን ደግሞ አሁን አዲስ ድጎማ ይዛ ብቅ ማለቷ ነው የተነገረው፡፡ ዴይሊ ሜል እንደዘገበው ከሆነ የሀገሪቱ ግሪን ፓርቲ መንግስት የዜጎችን የወሲብ ወጪ መሸፈን አለበት የሚል እቅድ አቅርቧል ብሏል፡፡

በጀርመን የወሲብ ንግድ ህጋዊ ዘርፍ መሆኑን የተናገረው ዴይሊ ሜል አንዳንድ ዜጎች ግን ወሲብ ለመግዛት አቅም እንደሚያጥራቸው ይተርካል፡፡ በጎረቤት ኔዘርላንድ ይህን መሰሉን ችግር መንግስት ለዜጎች ድጎማ በማድረግ እንደሚፈታ ያስታወቀው ዘገባው የጀርመኑ ግሪን ፓርቲ ጥያቄም ከዚህ እንደማይለይ ይናገራል፡፡

ወሲብ ከጭንቀትና ከአይምሮ ጤና ጋር በተያያዘ ለህክምና አገልግሎት በሀኪሞች መታዘዙ በጀርመን የተለመደ መሆኑን ያወራው ዘገባው ይሁን እንጂ በአቅም እጦት ይህን መድሀኒት መከታተል የማይችሉ ሰዎች መኖራቸውን ይናገራል፡፡

አሁን ላይ ግሪን ፓርቲ አቀረብኩት ያለው እቅድም ለነዚህ ዜጎች የድጎማ አቅርቦት መንግስት እንዲፈቅድ የሚያደርግ መሆኑን ዘገባው በሰፊው አብራርቷል፡፡ dailymail

READ  ዩጋንዳ የ 1.28 ቢሊዮን ዶላር የእርሻ ፕሮጀክት ልትሰራ ነው

NO COMMENTS