የእጅ ሙቀትን የሚጠቀም የሞባይል ቻርጀር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባል ተባለ

0
630

የእጅ ሙቀትን የሚጠቀም የሞባይል ቻርጀር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባል ተባለ- የአስራ ዘጠኝ ዓመት እድሜ ያለው  ቬጋም የተባለ ቤላሩሳዊ ወጣት ከሰውነታችን የሚወጣን  የሚቀት ሃይል ሃይልን የሚጠቀም የሞባይል ቻርጀር ፈጥሯል የሚለን ላይፍ ኢዝ ጉድ የተሰኘው የሬድዮ ፕሮግራም ቻርጀሩ ከእጃችን መንቀሳቀስ የሚመነጨውን ሙቀት ተጠቅሞ ሞባይሎችን ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችለውን ሃይል መሰብሰብ ይችላልም ብሏል፡፡

በተለይም የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በሞባይል ቻርጅ ቶሎ ማለቅ ምክንያት የሚቸገሩ በመሆኑ ይህ ቴክኖሎጂ እፎይታን ይሰጣል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኤሌክትሪክ ሃይል በሌለበት አካባቢ ለሚሮሩ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቀቃሚዎችም ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ይህ የእጅ እንቅስቃሴን እና ከዚያ ከሚወጣውን የሙቀት ሃይል ለሞባይል የሚያገለግል የኤሌክትሪክ ሃይል መፍጠር የሚችለው ቻርጀር አንድ ስማርት ስልክን ሙሉ ለሙሉ ቻርጅ ለማድረግ የሚወስድበት ግዜ አርባ ደቂቃ ብቻ መሆኑም የቴክኖሎጂውን ችግር ፈቺነት የሚያመላክት ነው፡፡

ይህን ፈጠራ ወደ ምርት ለማሸጋገር ሃምሳ ሺህ ዩሮ ያስፈልገው የነበረው ይህ ቤላሩሳዊ የአስራ ዘጠኝ ዓመት ወጣት የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮች እስከ ሰባ አንድ ሺህ ዩሮ ቃል ገብተውላታል ተብሏል፡፡

በቅርቡም ይህን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ለማስገባት ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን መናገሩም ተጠቁሟል፡፡

እስከ መጪው መጋቢት ድረስም ቻርጀሩን ወደ ተጠቃሚዎች ለማድረስም መታቀዱ ተሰምቷል፡፡

የሬድዮ ፕሮግራሙ አዘጋጆች ይህን መሰል ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ግዜ አይፈጅባቸውም ያሉ ሲሆን ምርቱ ይፋ በሆነ በአንድ ወር ውስጥም ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎች ይደርሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

የስማርት ስልኮችን መስፋፋት ተከትሎ የቻርጅ ቶሎ ቶሎ ማለቅ ችግርን ለመፍታ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ይፋ ሆነው ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ፓወር ባንክ አንዱ ሲሆን የዚህ የቤላሩሳዊ ወጣት ፈጠራ ግን ከዚህ ቀደም ከተፈጠሩት ሁሉ ቀላሉ እና ችግር ፈቺ ይሆናል የሚለው የብዙዎች ተስፋ ነው፡፡

READ  ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና ሃይማኖታዊ ስራዎቻቸው …

NO COMMENTS