‹‹አለመኖር›› የተሰኘው አነጋጋሪ መጽሃፍ ለምረቃ በቅቶ ውይይት ተደርጎበታል

0
812

‹‹አለመኖር›› የተሰኘው አነጋጋሪ መጽሃፍ ለምረቃ በቅቶ ውይይት ተደርጎበታል – በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ህክምና የትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰርና የትምህርት ክፍሉ ሃላፊ በሆኑት በዶክተር ዳዊት ወንድም አገኝ ተጽፎ ባለፈው ሳምንት ለንባብ የበቃው ‹‹አለመኖር›› የተሰኘው ወጥ ረጅም ልብ ወለድ መጽሃፍ ብዙዎችን ሲያነጋግርና ሲያወዛግብ ሰንብቶ ሰሞኑን ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው ባታ የባህል ምግብ አዳራሽ በደማቅ ስነስርዓት ተምወቋ፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይም ይኸው ‹‹አለመኖር›› የተሰኘው መጽሃፍ ለውይይት ቀርቦ በተለያዩ ባለሞያዎች የሂስ ምልከታና ዳሰሳቀርቦበታል፡፡

በተለይ የፍልስፍና ምሁሩ ዶክተር ዳኛቸው ፣ የአእምሮ መምህሩ ዶክተር መስፍን አርአያ፣ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ እና ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ በመጽሃፉ ዙሪያ ያዩትን ፣ የተሰማቸውን እና ያጤቱንትን ሁሉ ሂሳዊ ምልከታቸውን በመጽሃፉ ምረቃ ላይ ለተገኘው ታዳሚ አቅርበዋል ፡፡

ዶክተር ዳዊት ወንድም አገኝ በአሁኑ ወቅት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  በአእመሮ ህክምና ክፍል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ባለሞያ ናቸው፡፡

ዶክተር ዳዊት ፍልስፍና  በህክምና ፣ በአእምሮ ህክምናና በህክምና ስነ-ምግባር አስተምህሮ ላይ ሊኖረው በሚገባው ፋይዳ ላይ ያተኮረ የምርምር ዝንባሌ ያላቸው ምሁር ናቸው፡፡

የቀደመው ባህል ፣ ፖለቲካ ፣ ታሪክ ፣ ማህበራዊ ኑሮና የኢኮኖሚ ጥምረት በአሁን እና በወደፊ የጤና አገልግሎት ስርዓት ላይ ያላቸውን የወል ሚናም ይመረምራሉ፡፡

መጽሃፉ አርባ አራት ምእራፎች ያሉት ሲሆን ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት የገጽ ብዛት አለው፡፡

ከዚህ ቀደምም ‹‹ቤት የመቱ ሃሳቦች ›› የሚል ስያሜ ያለው የግጥም መድብል ለተደራሲያን አቅርበዋል ሲል የዘገበው ሪፖርተራችን ሺወንዙ መላኩ ነው፡፡

ዶክተር ዳዊት ወንድማገኝ በመጽሃፋቸው መግቢያ ላይ ‹‹ይህ መጽሃፍ ዓላማ አድርጎ የተነሳው የተለመደውን እና እውነት የሚመስለውን ሁሉ በመጠየቅ እና በማፍረስ ነው›› የሚል ጽሁፍ አስፍረዋል፡፡፡

READ  Bedilu Ayele with a big heart but Poor

በተጨማሪም ‹‹ዓላመዬም  መጠየቅ ነው ፡፡ በመጽሃፉ ውስጥ በጥያቄ ለተፈተሹት ሃሳቦች መልስ ባታገኙ እንዳይገርማችሁ መልሱ ለእናንተ የተተወ ነው! ›› በማለት እኛም መጠየቅን ከደፈርን መልሱ ጋር መድረስ እንደማያቅተን የጸና እምነታቸውን በማወጅ መጽሃፉን እንድናነብ ይጋብዛሉ፡

NO COMMENTS