ቻይናዊው ፕሮፌሰር ማኦ ዜዱንግን በመተቸታቸው ከስራ ተባረሩ

0
631
ቻይናዊው ፕሮፌሰር ማኦ ዜዱንግን
ግለሰቡ በማህበራዊ ገጽ ስለማኦ በጻፉት ጽሁፍ የተነሳ አይንህን ለአፈር የሚላቸው በዝቷል ተብሏል በማእከላዊ ቻይና በሚገኘው የሻንዶንግ ጂአንዙ ዩኒቨርሲቲ የስነጥበብ ፕሮፌሰር የሆኑት የ 62 አመቱ ዴንግ ዢአዎቻኦ በፈረንጆቹ ታህሳስ 26 ቀን በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ስለማኦ ይከትባሉ፡፡

ግለሰቡ በማህበራዊ ገጽ ስለማኦ በጻፉት ጽሁፍ የተነሳ አይንህን ለአፈር የሚላቸው በዝቷል ተብሏል
በማእከላዊ ቻይና በሚገኘው የሻንዶንግ ጂአንዙ ዩኒቨርሲቲ የስነጥበብ ፕሮፌሰር የሆኑት የ 62 አመቱ ዴንግ ዢአዎቻኦ በፈረንጆቹ ታህሳስ 26 ቀን በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ስለማኦ ይከትባሉ፡፡

የአሁኗ ቻይና መስራች አባትና አብዮታዊ መሪ ተደርገው የሚታዩት ማኦ ዜዱንግ 3 ሚሊዮን ህዝቦችን ለገደለው የቻይና ረሀብና 2 ሚሊዮኖችን ለቀጠፈው የባህል አብዮት ቀውስ ተጠያቂ ናቸው ሲሉ ፕሮፌሰሩ መጻፋቸው ተነግሯል፡፡

ይህ ጽሁፍ ከገጻቸው ላይ ቢሰረዝም የቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ የዌቦ በርካታ ተገልጋዮች ፎቶ አንስተው ስላስቀሩት ለብዙዎች ተሰራጭቷል፡፡ ጉዳዩን የዘገበው ሮይተርስም ቢሆን ይህ በምስል የተቀመጠው የፕሮፌሰሩ ጽሁፍ እንደደረሰው ነው ያመለከተው፡፡

በቻይና ይህን መሰል ትችት ማሰማት ያልተለመደ መሆኑን ሚናገረው ሮይተርስ ይህን ተከትሎ ፕሮፌሰሩ ከዩኒቨርሲቲ ስራቸው መባረራቸውን ዘግቧል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የምሁሩን መባረር በተመለከተ ያለው ነገር ባይኖርም የዩኒቨርሲቲው የኮሙኒስት ፓርቲ ኮሚቴ ግን ዴንግ የውሸት መረጃ አሰራጭተዋል ሲል መግለጫ አውጥቶባቸዋል፡፡

በጉዳዩ የተቆጡ የአካባቢው ሰዎች እኚህኑ ፕሮፌሰር በማውገዝ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸው ተነግሯል፡፡ ማኦን የሚጠላ የህዝብ ጠላት ነው ሲሉም ፕሮፌሰሩን አውግዘዋል፡፡

በቻይና ስለታሪክ ማውራት ከባድ ዋጋ የሚስከፍል ጉዳይ መሆኑን ሚናገረው ፈዘገባው መንግስት ታሪክ ብሎ ሚናገረውንና ሚስተምረውን ነገር ብቻ ዜጎች ተቀብለው ከመኖር የዘለለ ምርጫ እንደሌላቸው ይናገራል፡፡ reuters

READ  ሁለት ተማሪዎች እርስ በእርስ በመተኳከስ እራሳቸውን አጠፉ

NO COMMENTS