በኢትዮጵያ ዳግም ለተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያስፈላጋል ተባለ

0
607

በኢትዮጵያ ዳግም ለተከሰተው የድርቅ አደጋ  – ከመስከረም እስከ ህዳር በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች መዝነብ የነበረበት መደበኛ ዝናብ ባለመዝነቡ በኦሮሚያ ሶማሊያ እና በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝች ክልል የድርቅ አደጋ እንዲከሰት ማድረጉን የሲጂቲኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡

በዘገባው የእረሻ ሚኒስትሩ አቶ ምትኩ ካሳ ሲናገሩ እንደተሰማው የፌደራል መንግስት እና ድርቁ የተከሰተባቸው ክልላዊ መንግስታት ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎችን በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች እያቀረቡ ነው፡፡

የተለያየ የምግብ እህሎች ፣ ጥራ ጥሬዎች እና አልሚ ምግቦችም ለህጻናት እየተከፋፈለ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለሰዎች እና ለቤት እንስሳት የውሃ አቅርቦት እና የጤና አገልግሎት እየተሰጠ ከመሆኑ ባሻገር የትምህርት ቁሳቁስም እንዲዳረስ ተደርጓል ብለዋለው አቶ ምትኩ ካሳ፡፡

የዓለም የምግብ ድርጅት በእነዚህ አካባቢዎች ተጨማሪ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለድርቅ ተጋላጭ ሊሆን እንደሚችል ማስጠንቀቁም በዘገባው ተመልክቷ፡፡

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ድርጅት ተወካይ አማዶ አላሆሪ እንደሚሉት አካባቢው የቤት እንስስሳት በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ የመኖእ እና የውሃ አቅርቦት ጉዳይ ግዜ የሚሰጥ አይደለም ብለዋል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳትም መሞታቸው ተገልጧል፡፡

ይህ የድርቅ ክስተት ሀገሪቱ በባለፈው ዓመት አጋጥሟት ከነበረው የኢሊኖ የድርቅ አደጋ በሚገባ ሳታገግም መሆኑ አስቸጋሪ ያደርገዋል ተብሏ፡፡

የዓለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ እንደሚሉት አንድ የድርቅ አደጋ ከገጠመ በኋላ መልሶ ለማገገም እስከ አራት ዓመታተል ሊወስድ የሚችል ቢሆንም መንግስት እና አጋር ተቋማት በድርቅ ምላሽ ላይ ልምድ ያላቸው በመሆኑ በፍጥንት ድርቁ የሚያመጣውን ጉዳት መከላከል ይቻላል ፡፡

922 ሚሊዮን ዶላርም የድርቁ ተጎጂ ወገኖችን ለመታደግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

READ  አረና ትግራይ ፓርቲ ስብሰባዬ በመንግስት ታገደብኝ ሲል ቅሬታ አቀረበ

NO COMMENTS