በቺካጎ የተሰባሰቡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ደጋፊዎች ኦባማን ለቀጣይ አራት አመታት ዋሽንግተንን ቢመሩስ የሚል ጥያቄ አቀረቡ

0
1889
በቺካጎ የተሰባሰቡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ደጋፊዎች
በቺካጎ የተሰባሰቡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ደጋፊዎች ኦባማን ለቀጣይ አራት አመታት ዋሽንግተንን ቢመሩስ የሚል ጥያቄ ጠየቁ

ፕሬዚዳንት ኦባማ በቺካጎ የመጨረሻውን የስንብት ንግግራቸውን ሲያደርጉ በየትኛውም እድሜ እና ሁኔታ የሚገኙ አሜሪካውያን ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ እንዲመለከቱ እና የመደማመጥ ባህላቸውንም እንዲያስቀጥሉ ነው የጠየቁት።

ከስምንት አመት በፊት ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ከነበረችው አሜሪካ የአሁኗ “በየትኛውም መመዘኛ የተሻለች እና ጠንካራ ናት” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የአሜሪካ ዴሞክራሲ ልዩ ምልክት መሆኑን ጠቁመዋል። ፍትሃዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍል፣ የዘር ክፍፍል እና በእውነታ ላይ ያልተመሰረተ አስተያየት የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ስጋቶች መሆናቸውንም አንስተዋል።

ኦባማ በ2008 44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ ድላቸውን ባበሰሩባት ቺካጎ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት ያደረጉት ንግግር አዎንታዊ መልዕክቶች የተላለፉበት ነው ተብሏል።

በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት የረዷቸውን ወጣት አሜሪካውያን እና ማንኛውም በእኩልነት እና ሁሉን ተጠቃሚ የምታደርግ አሜሪካ እንድትፈጠር የሚተጉ ዜጎች ስልጣን ከመያዛቸው በፊት ከነበራቸው በበለጠ ተስፈኛ እንዳደረጓቸውም ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በዶናልድ ትራምፕ ለመተካት ጊዜው መቃረቡን ተከትሎ ሰጋት የገባቸው በቺካጎ የተሰባሰቡ ደጋፊዎቻቸው ኦባማን ለሌሎች አራት አመታት ዋሽንግተንን ቢመሩስ የሚል ጥያቄ አቅርበው “ይህን ማድረግ አልችልም፤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሁለት ጊዜ በላይ መመረጥ አይፈቅድም” ብለዋቸዋል።

ኦባማ በመዝጊያ ንግግራቸው በፕሬዚዳንታዊ ስልጣኔ አሜሪካውያንን በመጨረሻ የምጠይቀው “እኔ ለውጥ ለማምጣት ባለኝ አቅም ሳይሆን በራሳችሁ እንድትተማመኑ” ነው ብለዋል።

በዋይት ሀውስ የስንብት ንግግራቸውን የሚያደርጉት ቀዳማዊ እመቤት ሚሸል ኦባማንም አሞካሽተዋል።
የ55 አመቱ የአሜሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በ2008 ሀገሪቱን እንዲመሩ ሲመረጡ በተስፋ እና ለውጥ የተሞሉ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ተከታያቸው ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የኦባማ አሻራ ያረፈባቸውን የተወሰኑ ፖሊሲዎች እስርዛለሁ ብለዋል። ከ10 ቀናት በኋላም ቃለ መሀላ ፈፅመው በይፋ ሀገሪቱን መምራት ይጀምራሉ።theguardian

READ  በኮንሶ የነበረው ችግር እየተረጋጋ መጥቷል፤ ኮንሶ ወደ መደበኛ ሕይወቷ እየተመለሰች ነው

NO COMMENTS