የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊው የቱሪዝም ሳምንት ለ10ኛ ጊዜ መካሄድ ጀመረ

0
726
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊው የቱሪዝም ሳምንት
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ካምፓስ ነው፡፡ በየዓመቱ የሚካሄደው ተናፋቂው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ሳምንት ላይ ታድሟል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን የለቀቁ የሚናፍቁት ታላቅ ኩነት ሲል የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱን እንዲህ ያስቃኘናል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊው የቱሪዝም ሳምንት ለ10ኛ ጊዜ መካሄድ ጀመረ፡፡

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ካምፓስ ነው፡፡ በየዓመቱ የሚካሄደው ተናፋቂው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ሳምንት ላይ ታድሟል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲን የለቀቁ የሚናፍቁት ታላቅ ኩነት ሲል የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱን እንዲህ ያስቃኘናል፡፡)

የዛሬ አስር ዓመት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ተጀመረ፡፡ በየዓመቱ በልዩ ድባብ የሚከናወነው ዓመታዊው የቱሪዝም ሳምንት ተናፋቂ መሆን ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በዚህ መልኩ ተማሪዎች ከአስተማሪዎች ጋር ሽር ጉድ ብለው የሚያዘጋጁት ድግስ ለአስረኛ ጊዜ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ በቀጣዮቹ አምስት ቀናትም እንደ ደመቀ ይቀጥላል፡፡ ከጥር 1 እስከ ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚቆየው የዘንድሮው በዓል ዛሬ ከሰዓት በማራኪ ካምፓስ በድምቀት ተከፍቷል፡፡

የቱሪዝም ተደራሽነትን መሪ ቃሉ ያደረገው የዘንድሮው በዓል አንደበተ ርዕቱዋን የህግ ባለሙያና ገጣሚ የትነበርሽ ንጉሴን የመክፈቻው የክብር እንግዳ አድርጓል፡፡ የቱሪዝም ሳምንት ኩነቱን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ ዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ደረጃ ትምህርት በመስጠት የሀገራችን ፋና ወጊ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቅሰው ይህ የቱሪዝም ሳምንትም በርካታ ሀገራዊ ኩነትን በተግባር የሚወጡ ባለሙያዎች በማፍራት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዓሉን በየዓመቱ በመታሰቢያነት ለተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት ይሰጣል፡፡ በዚህ አግባብ ከዚህ ቀደም እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፣ የቱሪዝም አባቱ ሀብተስላሴ ታፈሰ፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ባለውለታው ልዑል ራስ መንገሻ ዩሐንስን ጨምሮ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ተቋማትን ዘክሮ ነበር፡፡

ዘንድሮም በተመሳሳይ የቱሪዝም ሳምንቱ መታሰቢያነት የሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ መስህቦች ባለውለታ ለሆነው እና ስሜን ፓርክን ከዩኔስኮ የመፋቅ አደጋ ለታደገው የኦስትሪያ ፕሮጀክት ተደርጓል፡፡

READ  በሞያሌ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ላይ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ አምስት የኦነግ አባላት ክስ ተመሰረተባቸው

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተለያዩ አካባቢዎችን በሚወክሉ ባህላዊ አለባበሶች ቅጥር ግቢያቸውን አድምቀውታል፡፡ የጎንደር ሆቴሎች ራሳቸውን የሚፈትሹበት የምግብ እና አቀራረብ ውድድርም ተካሂዷል፡፡ የቁንጅና ውድድር እና የባህላዊ ጨዋታዎች ድግሱ እንደቀጠለ ነው፡፡

እንደተናፈቀ ተጀምሮ እንደተናፈቀ የሚጠናቀቀው ይህ የቱሪዝም ሳምንት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተማሩ ታላቅ ትዝታን ጥሎ የሚያልፍ ዓመታዊ ኩነት ነው፡፡ አስገራሚው ነገር ደግሞ ለኩነት ማስተባበር የሚወስዱት ትምህርት የተግባር መለማመጃም መሆኑ ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች፣ የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር እና ታዋቂ አርቲስቶች ታድመዋል፡፡ ነገ ምሁራኑ ከተማሪዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚመክሩበት አውደ ጥናት ይቀጥላል፡፡ DIRETUBE NEWS

NO COMMENTS