የጋናው ፕሬዝደንት የኩረጃ ንግግር እና የአምስት እውቅ ሰዎች የኩረጃ ንግግሮች

0
928

የጋናው ፕሬዝደንት የኩረጃ ንግግር እና የአምስት እውቅ ሰዎች የኩረጃ ንግግሮች- ሰሞኑን በአለ ሲመታቸውን ያከበሩት የጋናው ፕሬዝደንት ናና አኩፎ የቀድሞውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ንግግርን እንደወረደ መጠቀማቸው በምእራባዊን ሚድያዎች የዘለፋ ውርጅብኝ እንዲወርድባቸው አድርጓል፡፡

በእርግጥም ፕሬዝደንቱ የቡሽን ንግግር ምንጭ ሳይጠቅሱ መጠቀማቸው በግልጽ የፕሬዝደንቱን እና የጆርጅ ቡሽ ንግግርን አነጻጽሮ እውነቱን መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚህ ቀደም በዓለለም ታዋቂ የሚባሉ የፖለቲካ ሰዎችንም ይህን መሰሉን ኩረጃ አድርገዋል በሚል ሲወቀሱ ተሰምቷል፡፡

እስቲ ለትውስታ ያህል የተወሰነውን እናስታውሳችሁ፡፡

  1. ሜለንያ ትራምፕ ከ ሚሼል ኦባማ

የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሚስት ማሌንያ ትራምፕ የቀድሞውን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሚስት ሚሼል ኦባማ እ.ኤ.አ በ2008 የተናገሩትን ንግግር ወስዳ ተናግራለች በሚል ወቀሳ ሲቀርብባት ነበር፡፡

  1. ጆ ባይደን ከ ኒሊ ኪኖክ

በአንድ ወቅት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት የነበሩት ጆ ባይደን የእንግሊዝ የሌበር ፓርቲ መሪን ንግግር ወደስደዋል በሚል በመገናኛ ብዙሃን ማብጠልጠል ደርሶባቸው ነበር፡፡

  1. ስቴፈን ሃርፕስ ከ ጆን ሃዋርድ

ካናዲያን አላይንስ የተባለ የካናዳ የፖለቲካ  ፓርቲ መሪ የነበሩት ስቴፈን ሃርፕስ እ.ኤ.አ በ2008 የአውስትራሊያ ፕሬዝደንት የነበሩትን ጆን ሃዋርድን ንግግር የካናዳ ጦር ሃይል ወደ ኢራቅ እንዲዘምት ጥሪ ባቀረቡበት ንግግራቸው እንደራሳቸው ተጠቅመውበታል ፡፡

  1. ባራክ ኦባማ ከዴቫል ፓትሪክ

በ2008 በባራክ ኦባማ እና በሂላሪ ክሊንተን መካከል በነበረው የምረጡኝ ክርክር ወቅት ባራክ ኦባማ የማሳጩቴ ገዢ የነበሩት የዴቪድ ፓትሪክን ንግግር ወስደዋል በሚል በሂላሪ የምርጫ አስተባባሪዎች ሲተቹ ነበር፡፡

  1. ሂላሪ ክሊንተን ከ ጆን ኤድዋርድስ

በ2008 የምረጡን ዘመቻ ግዜ ሂላሪ በ2004 የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝደንት እጩ የነበሩትን ጆን ኤድዋርድስን ንግግር ቀድተዋል ተብለው ተወቅሰዋል፡፡

READ  ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት በሰራሁት ስራ እኮራለሁ አሉ

NO COMMENTS