የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል ማድረግ የሚገቡን ቅድመ ጥንቃቄዎች

0
1832

የአጥንት መሳሳትን ለመከላከል ማድረግ የሚገቡን ቅድመ ጥንቃቄዎች
1) የአልኮል መጠጥ አለመውሰድ

አልኮል መጠጦችን በተደጋጋሚ መጠቀም  የሰውነታችንን ካልሲየም መጠን ስለሚቀንስ የአጥንት መሳሳትን ሊስከትልብን ይችላል፡፡ በመሆኑም የአልኮል አጠቃቀማችንን ገደብ ልንሰጠው ይገባል፡፡
2) ሲጋራን ማጤስ ማቆም

ሲጋራ ማጤስ  በደም ውስጥ የሚገኝን ካልሲየም መጠን በተመሳሳ በመቀነስ ለአጥንት መሳሳት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል ሲጋራን ከህይወታችን ልናስወግድ ይናል
3) ወተት እና የወተት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን ማዘውተር

ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ያላቸው ካልሲም መጠን ከፍተኛ በመሆኑ የአጥንት መሳሳትን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡


4) በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

ከወተት እና ከወተት ተዋጽኦ ባሻገር በካልሲየም የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ለአጥንት መሳሳት የመጋለጥ እድልን ይቀንሳሉ፡፡ በካልሲየም ከበለጸጉ ምግቦችን ቆስጣ እና አሣ የመሣሠሉትን መጥቀስ ቻላል
5) የጠዋት ፀሐይን መሞቅ

የጠዋት ጸሃይን መሞቅ  በሰውነታችን  ቫይታሚን ዲ እንዲመነጭና ካልሲየም ሰውነታችን እንዲወስድ ይረዳል
6) የሚወስዱትን የካፊን መጠን ይቀንሱ

ካፊን ካልሲየም ከሰውነታችን እንዲወጣ ስለሚያደርግ የምንወስደውን የካፌ መጠን መቀነስ ያስፈልጋል
7) ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ

ማንኛውም አይነት የሰውነት እንቅስቃሴ ለጤና ጠቃሚ መሆኑ እውነት ነው፡፡ የአጥንት መሳሳትን በተመለከተም ቀለል ያለ ሰውነት እንቅስቃሴ ለሰውነትዎን ጥንካሬ እና መፍታታትን ስለሚሰጥ በቀላሉ ወድቀው ለስብራት እንዳይጋለጡ ይረዳል

  1. ወደ ሐኪም በመሄድ ቅድመ ምርመራ ያድርጉ

በተለይ ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ ያሉ ሴቶች ምርመራ ቢያደርጉ ይመከራል፡

READ  በ2030 በየአመቱ ትንባሆ በማጨስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 8 ሚሊየን ይደርሳል - የአለም ጤና ድርጅት

NO COMMENTS