ከተደላደለ ህይወት ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት የገባው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች –

0
5882

ከተደላደለ ህይወት ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት የገባው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች – ጌታሁን መንግስቱ ተክሌ ይባላል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች በመሆን ከአሸናፊ ግርማ እና ከዮዳኖስ አባይ ጋር በአን ቡድን ተጫውቷል፡፡

የተወለደው በወንጂ ከተማ ልዩ ስሙ  ጆንያ ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካበባቢ ነው፡፡

የእግርኳስ ህይወቱንም የጀመረው ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ሲሆን የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወቱ የተጀመረው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሳለ በባዶ እግሩ ሲጫወት በተመለከተው በአሰልጣን ካሳሁን ተካ አማካኝነት መሆኑን ተጫዋቹ ይናገራል፡፡ አሰልጣኙ እግር ኳስ በባዶ እግሩ ሲጫወት አይቶት ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ተናግሯል፡፡

በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተጫዋቹ ከጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡

ጌታሁን መንግስቱ ለመጀመሪያ የተጫወተው ክለብ ለመድህን የእግር ኳስ ክለብ መሆኑን የሚናገረው ጌታሁን በመጀመሪያው ጨዋታው ሀትሪክ መስራቱ ለብሄራዊ ታዳጊ ቡድን አባል አንዲሆን እንዳስቻለውም ይናገራል፡፡ በወቅቱ የአሰልጣኝ ጋርዚያቶ ቡድን ውስጥም ተጫውቶ አልፏል፡፡ ከእነ ሮበን እና ማይክል ኢሴን ጋር በተመሳሳ የውድድር መድረክ ላይ የመጫወት እንድልም ያገኘ ተጫዋች ነው፡፡

ብዙም ሳይቆይ ለዋናው ብሄራዊ ቡድን መመረጡንም ያስረዳል፡፡

በየመን ለሚገኝ የእግር ኳስ ክለብም ስድስት ዓመት ተጫውቷል፡፡ በወቅቱ ከጥቅማ ጥቅም ውጪ አስር ሺህ ብር እና በእያንዳንዱ ጎልም ሃምሳ ዶላር ይከፈለው እንደነበር ተጫዋቹ ያስረዳል፡፡

በትውውቅ እና በትዳር ለ 14 ዓመታት አብረው ከቆዩት የትዳር አጋሩ ጋር በአሁኑ ሰዓት የተለያየ ሲሆን ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጉ አሳዘኝ ክስተት ሆኗል፡፡

የመን ሰርቶ ባገኘው ገንዘብ የንግድ እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረ ሲሆን ከባለቤቱ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ለማብረድ መታህራ ደርሶ ሲመለስ ምንም አይነት ንብረት እንዳላገኘ እና በአሁኑ ሰዓት የጎዳና ህይወትን እየመራ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡

READ  የመከላከያና የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ 2ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቀቀ

የነበረው ንብረት እና ገንዘብ በባለቤቱ ስም የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ባለቤቱ በጀርመን ሀገር እንደምትገኝ ተናግሯል፡፡ ከዚህ በኋላም ወደ አሰልጣኝነት ህይወት መግባት ፍላጎቱ እንደሆነም ተባግሯል፡፡

በመጨረሻም የተጫዋጩን ህይወት ወደነበረበት ሊመልሱ የሚችሉ እገዛዎች ከተለያዩ ተቋማት እና ድርጅቶች ተደርገውለታል፡፡

ተጫዋቹን መርዳት እና ማገዝ ለሚፈልጉም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 10001190966406 እገዛ ማድረግ እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

NO COMMENTS