በ 40 አመታት የሚበላለጡት ጥንዶች ፍቅራችን በእድሜ አይገታም ሲሉ ቤተሰብ እንደሚመሰርቱ አስታወቁ

0
1775
በ 40 አመታት የሚበላለጡት ጥንዶች ፍቅራችን በእድሜ አይገታም ሲሉ ቤተሰብ
ድምጻዊ ሮብ ቴይለር የዛሬ 2 አመት በአሜሪካ ፔንሲልቫኒያ በአንድ ምሽት ክበብ ሲያቀነቅን እንዳየችው ነበር ልጅት ኤሪካ ጋወር በፍቅሩ የተነደፈችው፡፡ ሁለቱ ሰዎች መቀራረብ ቢጀምሩም በመሀከላቸው ግን ረጅም የእድሜ ድልድይ ነበር፡፡ ሮብ የ 64 አመት አዛውንት ሲሆን የ 24 አመቷን ወጣት ኤሪካን በ 40 አመታት የሚበልጥና አያቷ ሊሆን የሚችል ሰው ነበር፡፡

ድምጻዊ ሮብ ቴይለር የዛሬ 2 አመት በአሜሪካ ፔንሲልቫኒያ በአንድ ምሽት ክበብ ሲያቀነቅን እንዳየችው ነበር ልጅት ኤሪካ ጋወር በፍቅሩ የተነደፈችው፡፡ ሁለቱ ሰዎች መቀራረብ ቢጀምሩም በመሀከላቸው ግን ረጅም የእድሜ ድልድይ ነበር፡፡

ሮብ የ 64 አመት አዛውንት ሲሆን የ 24 አመቷን ወጣት ኤሪካን በ 40 አመታት የሚበልጥና አያቷ ሊሆን የሚችል ሰው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ያልበገራቸው እነዚህ ጥንዶች ግን ከተገናኙ ከ 6 ወራት በኋላ መተጫጨታቸውን አውጀው የወሬ ርእስ ለመሆን እንደበቁ ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡

አሁን ደግሞ ሁለቱ ጥንዶች ቤተሰብ ለመመስረት እቅድ እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል ነው የተባለው፡፡ ሮብን ገና ስታየው በፍቅር እንደወደቀችለት የምትናገረው ኤሪካ መጀመሪያ ያፈቀረችው ሰው እድሜው ግፋ ቢል ከ 40ዎቹ እንደማይዘል ገምታ እንደነበር ትናገራለች፡፡

የእጮኛዋ እድሜ 64 መሆኑን ካወቀችም በኋላ ለእርሱ ያላት ስሜት አለመቀዝቀዙን በመግለጽ ከዚህ ሽማግሌ ጋር ምን ሲደረግ ለሚሉ ተቺዎች መልስ የምትሰጠው ልጅት አሁን ላይ ካፈቀረችው ሰው ጋር ልጆች ወልዳ ለመሳምና ቤተሰብ ለመመስረት መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡ ሮብም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ፍጹም ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል ተብሏል፡፡

 

ብዙዎች የሁለቱ ሰዎች የእድሜ ልዩነት ሰፊ እንደሆነ በመጥቀስ ግንኙነታቸውን በክፉ ቢያዩትም እነርሱ ግን ፍቅር ከእድሜ ልዩነት በላይ ነው በሚል የበለጠ መዋደዳቸውና ቤተሰብ ስለመመስረት ማሰባቸው በእጅጉ ማስገረሙን ዘገባው ገልጿል፡፡dailymail

READ  ኢትዮጵያ የግብጽና የሱዳንን የውሀ ጥቅሞች ባልጎዳ መንገድ የህዳሴ ግድብን እንደምትገነባ አስታወቀች

NO COMMENTS