በእርግዝና ወቅት በነፍሰጡር ሴቶች የሚጠየቁ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና የህክምና ምላሾቻቸው

0
999

በእርግዝና ወቅት በነፍሰጡር ሴቶች የሚጠየቁ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና የህክምና ምላሾቻቸው – በእርግዝና ወቅት በተለይም በመጀመሪያ የእርግዝና ወቅት ነፍሰጡር ሴቶች በርካታ ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ፡፡

በኢትዮፒካሊንክ መረጃ አምስት በተባለው የመረጃ ፕሮግራም ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሚጠይቋቸው አምስት ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ? ምላሾቹስ ? በሚል የቀረበውን መረጃ በዚህ አይነት መልኩ አቅርበንላችኋል፡፡

ጥያቄ 1. የስፖርት (አካላዊ እንቅስቃሴ)መስራት እችላለሁ ወይ ?

በርካታ የህክምና ባለሞያዎች ጤናማ የሆነ የእርግዝና ግዜ እንዲኖረን እና በምጥ ወቅት የሚከሰትን ከፍተኛ ህመም ለመቀነስ የአካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ጠቃሚ መሆኑ ቢጠቆምም ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሚከታተላቸውን የህክምና ባለሞያ አማክረው የሚሰሩትን እንቅስቃሴ አይነት ማወቅ ይጠበቅባቸዋል ይላል መረጃው፡፡

ጥያቄ 2. ስቲም ፣ ሳውና መግባት እና በሞቀ ውሃ መታጠብ ችግር ያመጫል ?

እጅግ ባልሞቀ ውሃ መታጠብ ችግር እንደማያመጣ ነገር በታም በፈላ ውሃ መታጠብ እና ለረዥም ግዜ የሞቀ ውሃ ውስጥ መዘፍዘፍ  አይመከርም ይላል መረጃው፡፡ ሳውና እና ስቲምን በተመለከተ ላልተራዘመ ግዜ ወይም እስከ 20 ደቂቃ ለሚደርስ ግዜ ነሆነ ችግር የለውም ተብሏል፡፡ ከዚህ ከበዛ ግን ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ጥያቄ 3. የራጅ ምርመራ ማካሄድ ጽንሱን አይጎዳውም ወይ ?

የራጅ ምርመራ ማድረግ አልፎ አልፎ ችግር ሊመጣ ቢችልም እንደሚፈራው ያህል ጉዳት አያመጣም ተብሏል፡፡

ጉዳት ሊያመጣ ይችላል የተባለው የራጅ ምርመራ አይነት የጥርስ ራጅ ምርመራ ሲሆን እጅር አጣዳፊ ካልሆነ በእርግዝና ወራት ይህን ምርመራ ማድረግ አይመከርም፡፡

በከዚህ በተለየ እግዝና ወቅት  የራጅ ምርመራ ማድረግ ይህ ነው የሚባል ጉዳት አያደርስም ይላል መረጃው ፡፡ ነገር ግን ምርመራው በትክክለኛው ሙያተኛ መካሄድ ይኖርበታልም ይለል፡፡

READ  Beckham Works towards Ending HIV/AIDS Pandemic in Ethiopia

ጥያቄ 4. ስራ መስራት ችግር ያመጣል ወይ

ኬሚካል ያለባቸው እና ለጨርር የተጋለጡ የስራ መስኮች ለነፍሰጡር ሴቶች አይመከርም የተባለ ሆን ከዚህ ውጪ ያሉ ሌሎች ስራዎች ለእርግዝና ችግር እንደማያመጡ ነገር ግን ለረዥም ግዜ ቆሞ የሚሰራ ስራ ከሆነ ግን ከሶስት ወር በላይ ይህን መሰል ስራ መስራት ለነፍጸጡር ሴቶች አይመከርም ተብሏል፡፡

ጥያቄ 5 ቡና (ካፌን) መጠቀም፣ ለአደጋ ያጋልጣል ወይ ?

መጠነኛ ቡና መጠጣት ወይም በቀን ከሶስት ስኒ በታች የሆነ ቡናን መጠጣት ጉዳት የማያመጣ ቢሆንም ከአምስት ስኒ በላይ ቡና የሚጠጡ እና ከፍተኛ የካፌን መጠን ያላቸውን ምግቦች በከፍተኛ መጠን መመገብ ላልተፈለገ ውርጃ ሊያጋልጥ ይችላል ተብሏል፡፡ ካፌን የተባለው ንጥረ ነገር ለነፍሰጡሯም ሆነ ለህጻኑ አስፈላጊ የሆኑትን ካልሲየም እና አይረን የተባሉትን ንጥረነገሮች ስለሚወስድ ነፍሰጡር ሴቶች የካፌን አጠቃቀማቸውን መመጠን ይኖርባቸዋል፡፡

NO COMMENTS