ሳዑዲ ለ375 ኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት አደረገች

0
3520
ሳዑዲ ለ375 ኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት አደረገች
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው ለነበሩ 375 ኢትዮጵያውያን ምህረት ማድረጉን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው ለነበሩ 375 ኢትዮጵያውያን ምህረት ማድረጉን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለእስረኞች ምህረት የተደረገው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የ1437 ዓመት ሂጅራ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ፥ ለሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ጠባቂ ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ጠቁሟል።

በሳዑዲ ዓረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አሚን አብዱልቃድር፥ ሳዑዲ በቁጥጥር ስር ለነበሩ ኢትዮጵውያን እስረኞች ምህረት ማድርጓ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መጠናከሩን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ላለፉት አራት አመታት በተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያውያን ምህረት መደረጉ በመግለጫው ተጠቅሷል።
በሁለቱ ሀገሮች የግንኙነት ታሪክ ለኢትዮጵያውያን እስረኞች ምህረት ሲደረግ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው።

READ  ሂላሪ ክሊንተን ከዶናልድ ትራምፕ በተሻለ ከፍተኛ ድምፅ እንዳገኙ ያውቃሉ

NO COMMENTS