‹‹ትክክለኛ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ›› ተገኘ መባሉ ብዙዎችን እያወዛገበ ይገኛል

0
7051

‹‹ትክክለኛ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ›› ተገኘ መባሉ ብዙዎችን እያወዛገበ ይገኛል – ሪቻርድ ኒቭ የተባሉ ሳይንቲስት ትክክለኛው የእየሱስ ክርስቶስ ገጽታ በሚል አንድ ምስል ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተለያዩ የተቃውሞ ድምጾች እና የተለያዩ አስተያየቶች እየሰተሙ ይገኛሉ፡፡

እንደ ሰይንቲቱ አገላለጽ ከሆነ ከዚህ ቀደም በዓለም ላይ የሚታወቀው የእየሱስ ክርስቶስ ምስል በፍጹም ከክርስቶስ ጋር አይመሳሰልም የሚል ሃሳብን ማንጸባረቁ ግርምትን እና ክርክርን ፈጥሯል፡፡

ሪቻርድ ኒቭ የተባሉት እኚሁ ግለሰብ ‹‹ትክክለኛ ነው ›› ያሉትን የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ለማግኘት የተለያዩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን ተጠቅሚያለሁ ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ እየሱሰስ ክርስቶስ የአኗኗር ዘይቤን እና የህይወት መርህን ለሰዎች ያስረዳበት የነበረው መንገድ እንዲሁም በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን የአካላዊ ገጽታ ተክለ ሰውነት ይገኙበታል፡፡

እኚሁ ሳይንቲስት ይህን በእሳቸው አባባል ‹‹ትክክለኛ›› ነው ያሉትን የኢየሱስ ክርስቶስ ምስልን ለማግኘት ከ1998 ጀምሮ ጥናት አካሂጃለሁ ማለታቸው እና በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ የሰው ልጆች የራስ ቅልን ለምርምሬ ተጠቅሚያለሁ ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡

‹‹ትክክለኛው›› የእሱስ ክርስቶስ ምስል ተብሎ በቢቢሲ በቀረበው ዶክመንተሪ  የታየው ምስል ከዚህ በፊት እየሱስ ክርስቶስ ነው ተብሎ በርካቶች የሃይማኖት ተቋማት ይጠቀሙበት ከነበረው ምስል ጋር ምንም አይነት ተመሳሳይነት የሌለው ነው፡፡

በዚህም ይመስላል ከበርካታ የእየሱስ ክርስስ ተከታይ ወገኖች የተቃውሞ ድምጽ እየተሰማ የሚገኘው፡፡

READ  ስለ ዘርፈ ብዙው ባለሞያ አበበ ባልቻ ያልተሰሙ እና አስገራሚ አስር እውነቶች

NO COMMENTS