ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ የሚመገበው ጥምዝ ህንጻ

0
1726

ታይዋን ካርቦንዳይ ኦክሳይድን የሚመገብ ህንጻ በ2017 ይፋ ልታደርግ ነው፡፡

ህንጻው ታኦ ዡ ይን ዩዋን ይባላል፤ ካርቦን ተመጋቢ ህንፃ በታይዋን ዋና ከተማ ታይፒ በቪንሴንት ኮልባውት በሚመሩ የስነ ህንፃ ባለሙያዎች በፈረንጆች መስከረም 2017 እንደሚጠናቀቅም ተነግሯል፡፡

በዓለማችን ከሚገኙ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች በአካባቢ ጥበቃው ወደር የለሽ ይሆናል የተባለው “ታኦ ዡ ይን ዩዋን” ህንጻ በየደረጃው አራት ነጥብ አምስት ድግሪ እንደሚሽከረከርም ነው የተሰማው፡፡

የታይፔን ከተማ ከአራቱም አቅጣጫ ከጫፍ እስከ ጫፍ ለመቃኘት የሚያስችል ከፍታ ያለው ሲሆን፥ የብዝሃ ሕይወትን ለመጠበቅ አልሞ ነው በመገንባት ላይ ያለው።

ይህ ህንጻ በዙሪያው እና በውስጡ 23 ሺህ ዛፎች የሚኖሩት ሲሆን፥ በዓመት ዓለምን የሚበክል 130 ቶን የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀትን መጥጦ እንደሚያስቀር ይጠበቃል፡፡

የስነ ህንጻ ባለሙያው ቪንሴንት ኮልባውት ራዕያቸው ታይፔ የአረንጓዴ ልማት እና የስርዓተ ምህዳር ደህንነት መገለጫ እንደመሆኗ ይህን የሚያስጠብቅ ረዥም ህንጻ መገንባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ታኦ ዡ ይን ዩዋን” ህንጻ የራሱ የመተንፈሻ አካላት የሚኖሩት ሲሆን የአረንጓዴ ዘላቂ ልማትን ለመጠበቅ እና የመሬት መንቀጥቀጥን ለመከላከል ሁለት ዩኒቶች በየወለሉ እንደሚገጠሙ ተጠቅሷል፡፡

ተፈጥሯዊ እፅዋቶችን ጨምሮ ሌሎች የካርቦንዳይ ኦክሳይድን የሚመገቡ የህንጻ ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን፥ ግንበኞችን ሊያስቸግር የሚችለው የግንባታው ክፍል ይህ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የፀሃይ ብርሃን፣ የእንፋሎት ሃይል እና የነፋስ ሃይል የብዝሃ ሕይወት እና የአየር ንብረትን የሚያስጠብቁ የህንጻው የሃይል ምንጮች ለማድረግ ታቅዷ፡፡

የህንጻው ምድረ ገቢም 6 ሺህ 60 ስኩዌር ሜትር በሚሸፍኑ እፅዋት ይሸፈናል ተብሏል።

READ  የእጅ ሙቀትን የሚጠቀም የሞባይል ቻርጀር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባል ተባለ

NO COMMENTS