‹‹ኢትዮጵያዊ›› ኮንሰርት ካሰገባው ገቢ ግማሽ ያህሉን ለእርዳታ ሰጠ

0
2018

‹‹ኢትዮጵያዊ›› ኮንሰርት ካሰገባው ገቢ ግማሽ ያህሉን ለእርዳታ ሰጠ –በገና ዋዜማ በላፍቶ ሞል የተካሄደው እና ተወዳጅ የሙዚቃ ሰዎች የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት ‹‹ኢትዮጵያዊ›› የተሰኘው ኮንሰርት ካስገኘው ገቢ ሃምሳ በመቶ የሚሆነውን ጌርጌሶናዊያን ለተባለ እና በአእምሮ ህመምተኞች ላይ ለሚሰራ የበጎ አድራጎት ተቋም መስጠቱ ተነግሯል፡፡

የሐበሻ ቢራ ማርኬቲንግ ማናጀር የሆኑት አቶ ጌታነህ አሰፋው በታዲያስ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ በስልክ እንደተናገሩት በኮንሰርቱ ከተገኘውን ገቢ ግማሽ ያህሉን ለጌርጌሶናዊያን በጎ አድራጎት ተቋም በልገሳ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

ይህ የልገሳ ስራም ለሐበሻ ቢራ የመጀመሪያው እንዳልሆነ እና ከዚህ ቀደምም መሰል በተለያዩ ግዚያት ለተለያዩ አካላት የማህበራዊ ድጋፎችን መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ጌርጌሶናዊያን የእርዳታ ተቋም የገጠመውን ችግር አይተን ይህን ልገሳ አድርገናል ያሉት የሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር የማርኬቲንግ ሃላፊ ወደ ፊትም ከተሙ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ እና በሌሎች የማህበረሰብ ፣ የስፖርት እና መሰል ጉዳዮች ላይ ድጋፉ እየሰጠን እንቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ጌታነህ መሰል ተግባር የሐበሻነት መገለጫ ነውም ብለዋል፡፡

ይህ ኮንሰርት በጆርካ ኤቨንት ኦርጋናይዘር እና በሐበሻ ቢራ ትብብር የተካሄደ ሲሆን ድምጻዊያን ቤቲ ጂ ፣ ልጅ ሚካኤል ፣ ሳሚ ጎ እና ሌሎች እውቅ ድመጻዊያን ተሳትፈውበት ነበር፡፡

ለዚህ ዝግጅትም ከፍተኛ የሚባል ወጪ እንደተደረገበት መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

 

READ  በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ድንበር አቋርጠው ለመውጣት የሞከሩ 105 ሰዎች ተያዙ

NO COMMENTS