አርቲስት ይርዳው ጤናው በታዲያስ አዲስ የገና በዓል ፕሮግራም አዲስ አልበሜን ጠብቁ ብሏል

0
204

አርቲስት ይርዳው ጤናው በታዲያስ አዲስ የገና በዓል ፕሮግራም አዲስ አልበሜን ጠብቁ ብሏል – ተወዳጁ ድምጻዊ  እና ኮሜዲያን ይርዳው ጤናው በገና በዓል በታዲያስ አዲስ ከጋዜጠኛ ጸገነት እና ከታደለ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡

የድምጻዊው ነጠላ ዜማም በፕሮግራሙ ተሰምቷል፡፡ በቅርቡም አዲስ አልበም እንደሚያወጣ ተናግሯል፡፡

የኑሮ ሁኔታውን በተመለከተ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እና ካናዳ እየተመላለሰ እንደሚኖር እና የተለያዩ ሀገራት ለስር እንደሚዘዋወርም አብራርቷል፡፡

የአርሰናል የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ የሆነበትን አጋጣሚ ሲያብራራ እግርኳስ የሚያዩ ጓደኞቹ በጨዋታ ወቅት ስለ አርሰናል አጨዋወት እየነገሩት የአርሰናል ደጋፊ ሆኛለሁ ብሏል፡፡

‹‹ለማላየው ነገር ለምንድነው የምቃጠለው ? ›› ብሎም በራሱ ላይ ቀልዷል፡፡

ኮሜዲያን ይርዳው ጤናው ስለ ኮሜዲያን ተስፋዬ ካሳ አንስቶም የተለያዩ ቀልዶችን ጨዋታዎችን ተጨዋውቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር በቤቱ ግብዣ አድርጎለት እንደነበረ እና የድምታዊው አዲስ አልበምም ተወዳጅ እንደሚሆን ጠቆም አድርጓል፡፡

ድምጻዊ እና ኮሜድያን ይርዳው ጤናው ከዚህ ቀደም ሁለት አልበሞች ያሉት ሲሆን ሁለተኛ አልበሙ ከፍተኛ የህዝብ ተቀባይነት አግኝቶ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ይርዳው በቀልድ ስራዎችም ዝናን ካተረፉ እና በግንባር ቀደምትነት ከሚጠሩ ኢትዮጵያዊን ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱ ለመሆን የቻለ እና በተለየ መልኩ በራሱ ላይ በመቀለድ እና የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችን ድምጽ በማስመስል ይታወቃል፡፡

READ  ጫት ባለፉት አምስት ወራት 120 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል ተባለ

NO COMMENTS