ለ 44 ዓመታት በቤተ መንግስት በሬ አራጅነት

0
302

ለ 44 ዓመታት በቤተ መንግስት በበሬ አራጅነት – ቤተ መንግስት ሲታሰብ በውስጡ ይኖራሉ ብለን በምናብ የመንስላቸው ባለስልጣን ሃላፊውን እና ጠባቂዎቻቸውን ይሆናል፡፡

ነገር ግን በቤተ መንግስት የተለያዩ ሙያ ያሏቸው ግለሰቦች በሙያቸው ያገለግላሉ፡፡ ከዚህ ቀደምም ለበርካታ ዓመታት በቤተ መንግስት ጸጉር ቆራጭነት ስላገለገሉ ሰው ሰምተናል፡፡

የገና በዓል የኢቢሲ የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳ የቤተ መንገስት ሰራተኛ እና በሬ አራጅ የነበሩ ናቸው፡፡ በሙያቸውም ለ አርባ አራት ዓመታት በዚያው በቤተ መንግሰት አገልግለዋል፡፡

አቶ ገብረ መድህን ይባላሉ በ1949 ዓ.ም በአሰላፊነት የስራ መደብ በቤተ መንግስት እንደተቀጠሩ እና በኋላ ላይም ለሁለት ዓመት ስልጠና ተሰጥቷቸው በሬ አራጅ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

በወቅቱ ለስራው የተመረጡት ‹‹ጉልበት አላቸው›› በሚል አካላዊ ቁመናቸው ታይቶ እንደነበረም ያስታውሳሉ አቶ ገብረ መድህን፡፡

ከአጼ ሃይለስላሴ ጋር በአካል ተገናኝቼ ነበር የሚሉት አቶ ገ/መድህን አጼ ሃይለስላሴ የበግ እንጂ የበሬ ስጋ እንደማበሉም አስታውሰዋል፡፡

በኮሎኔል መንግስቱ ግዜም ‹‹እርድ አያስፈልግም›› ተብሎ ስጋ ከቄራ ይመጣ ነበረ ብለዋል፡፡

አቶ ገ/መድህን ከባለቤታቸው ጋር እዛው ቤተ መንግስት ተዋውቀው ከሃምሳ ዓመታት በላይ  ሳይለያዩ በፍቅር እንደኖሩ እና የአንድ ብር እቁብ እንደነበራቸው በወቅቱም ሰባት ክፍል ያለው ቪላ ቤት በ አራት ሺህ አምስት መቶ ብር መግዛታቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለቤታቸው በስራ ጉዳይ ከአጼ ሀይለ ስላሴ ጋር የተለያዩ ቦታዎች መሄዳቸውንም ተናግረዋል፡፡

READ  “ዛፍ መሳይ እጅ ያለው” በመባል ዓለምን ያነጋገረ የ27 ዓመት የባንግላዲሽ ዜጋ

NO COMMENTS