የፍቅር በዓል የሆነው የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን በመተሳሰብና በአንድነት ማክበር ይገባል – የሀይማኖት አባቶች

0
785
የፍቅር በዓል የሆነው የእየሱስ ክርስቶስን ልደት
ፍቅር በዓል የሆነው የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን በመተሳሰብና በአንድነት ማክበር ይገባል

የፍቅር በዓል የሆነው የእየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን በመተሳሰብና በአንድነት ማክበር እንደሚገባ የሃይማኖት መሪዎች አሳሰቡ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ህብረትና የኢትዮጵያ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን መሪዎች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለምዕመኖቻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፥ በዓሉ እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ወደ ምድር በመምጣት የገለጸበት እንደመሆኑ በሰው ልጆች መካከል ጥልቅ የሆነ ፍቅር መቻቻልና መከባበር እንዲሰፍን ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ፓትርያርኩ እንዳሉት በሰው ልጆች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ሁሉም ለአንድነት፣ እኩልነት፣ ለወንድማማችነት፣ ለመተማመንና ለመከባበር የጋራ አቋም ሊይዝ ይገባል።

የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ዋና አላማም መለያየትና መቃቃርን በጥላቻ አይን መተያየትን አስወግዶ በምትኩ ለሰው ልጆች ሁሉ የሚሆን ዘላቂ ሰላምና አንድነትን ለማስፈን መሆኑንም ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀዻዻሳት ብጹዕ አቡነ ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ሱራፌልም፥ የክርስቶስ መወለድን ስናከብር እናቶችና ህጻናትን በማስታወስ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍንና የሀገሪቱ የእድገት ጉዞ እንዳይገታ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን መወጣት ይኖርበታል ያሉት ደግሞ፥ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ናቸው።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው በሀገሪቱ ያለው ሰላም እንዲቀጥል ሁሉም ምዕመን የየራሱን ሚና ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ መካነ እየሱስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ቄስ ዶክተር ዋቅስዩም ኢዶሳ ባስተላለፉት መልዕክት ደግሞ፥ ምዕመናኑ የቤተሰብ በዓል የሆነው የክርስቶን የልደት በዓል ሲያከብር ለሌላቸው ወገኖች በማካፈልና እርስ በርስ በመረዳዳት መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

READ  ኮሜዲያን ፍልፍሉ እና ደምስ በገና የበዓል የመዝናኛ ፕሮግራም

የሃይማኖት መሪዎቹ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። ኤፍቢሲ

NO COMMENTS