የገና ጨዋታ እና ታሪካዊ ዳራው …

0
678

የገና ጨዋታ እና ታሪካዊ ዳራው  – ከትውልድ ትውልደ እየተላለፈ እዚህ የደረሰው የገና ጨዋታ በሀገራችን ጥንታዊ ከሆኑ ባህላዊ ትውፊቶች ውስጥ አንዱ ስለመሆኑ ጥንታዊ የብራናዎች እና የግድግዳ ላይ ጥንታዊ ስእሎች ምስክር ናቸው፡፡

የዚህ ባህላዊ ጨዋታ አመጣጥን አስመልክቶ ሁለት የተለያዩ ትውፊታዊ ባህሎች እንደሚነገሩም በአንድ ወቅት ከኢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት ጸሃፊ እና የታሪክ ተመራማሪ መምህር ካህሳይ ገ/ሄር ያስረዳሉ፡፡

የታሪክ ተመራማሪው የመጀመሪያው እረኞች ጌታ በተወለደ ግዜ መላእኩ ቅዱስ ገብርኬል በነገራቸው መሰረት አብረው እዛወ ተገኝተው ከመላእክቱ ጋርም አብረው ዘምረዋል፡፡ እነዚህ እረኞች በወቅቱ የገና ጨዋታ ይጫወቱ ነበር የሚለው አንድ ራሱን የቻለ ትውደፊት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ሁለተኛው ሄሮደስ ሰባ ሰገል ወደ ጌታ ሲሄዱ ከእነሱ ጋር አመሳስሎ ሰላይ መላኩን እና ሰባሰገሎቹን እና ወታደሮቻቸውን የሚመራቸውም ኮከብ ቀጥ ብሎ መቆሙን በዚህም ግዜ  ግዜ ሰባ ሰገሉ ራሳችንን እንፈትሽ ብለው ሲፈትሹ ሰላዩ እንደተያዘ እና አንገቱ በሰይፍ ተቀልቶ ጭንቅላቱን እንደ ገና ከኳስ እንደተጫወቱበት እና ጨዋታውም በዛው ተጀመረ የሚለው ሁለተኛው ትውፊት እነደሆነም ምሁሩ ያብራራሉ፡፡

የገና መጫወቻ በትር ሽልምልም መሆኑን ከያቆብ በትር ጋር የሚያይዘው ነገር መኖሩም ይገለጻል፡፡ከተለያዩ ከማይሰበሩ የዛፍ አይነቶችም ይሰራሉ፡፡

‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የሚለው አባባልም ጌታ ወደ ምድር የመጣው ሁሉንም እኩል ለማድረግ መሆኑን አስመልክቶ መሆኑን መምህር ካህሳይ ገ/ሄር ያስረዳሉ፡፡

የገና ጨዋታን ተጨማሪ የታሪክ ዳራውን መከታተል ይችላሉ

READ  ድሬቲዩብ ለድምጻውያን በዩቱብ ገቢ እንዲያገኙ በማድረግ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው

NO COMMENTS