የገና በዓል ገበያ አምና እና ዘንድሮ ምን ይመስላል …. ?

0
149

የገና በዓል ገበያ አምና እና ዘንድሮ …. በበዓላት ወቅት የበግ እና የዶሮ እንዲሁም የበሬ ገበያ ከየትኛውም ግዜ በላይ የሚደራበት ወቅት ነው፡፡

በባለፈው ዓመት የገና በዓል የበሬ የመግዣ ዋጋ ከትንሹ ከ አምስት ሺ ብር ጀምሮ ትልቅ እስከሚባለው ሃያ አምስት ሺህ ብር ይደርስ እንደነበር በወቅቱ የቀረበ አንድ የቢዝነስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የአምናውን የገና በዓል የበግ መግዣም አስመልክቶ ዘገባው በተለያዩ ገበያዎች በመዘዋወር የሰበሰበው መረጃ ከ አንድ ሺ አራት መቶ ብር እስከ አራት ሺህ ብር ርርስ እንደነበር ያስረዳል፡፡

የዶሮ ዋጋ ደግሞ በወቅቱ በአዲሱ ገበያ የሾላ ገበያ ዋጋ ከመቶ ሃምሳ እስከ መቶ ሰማንያ ብር እንደነበረ እና ይህም እንደተወደደባቸው ገዢዎች ተናግረው ነበር፡፡በተመሳሳይ ወቅት በኤልፎራ የአንድ ዶሮ ዋጋ አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ብር እንደነበረም ይህ ዘገባ አትቶ ነበር፡፡

በዛው በአምናው የገና ሰሞን የሽንኩርት ዋጋም ከአስራ አንድ ብር እስከ አስራ ሶስት ብር ሲሸጥ ነበር እንደ ዘገባው ዳሰሳ፡፡

በሌላ በኩል በዘንድሮው የገና በዓል መሰል ዋጋዎችን የተመለከተ ሌላ ዘገባ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡

በዘንድሮው ገበያ የዶሮ መግዣ ዋጋ ከ ሁለት መቶ ብር እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ሆኖ መቆየቱ ከተለያዩ ሸማቾች ተሰምቷል፡፡

የበግ ዋጋንም ስንመለከት ከትንሹ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብት ጀምሮ እስከ ሶስት ሺ አምስት መቶ ብር ድረስ መሸጡን ሰምተናል፡፡

ሽንኩርትም ከስምንት እስከ አስር ብር መሸጡን እንዲሁም የዶሮ ዋጋም ከሁለት መቶ እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር መሆኑን ሸማቾች ገልጸዋል፡፡

የእናንተን የገበያ ውሎ አካፍሉን

READ  Ethiopia Tops as Fastest Growing Country in the World

NO COMMENTS