የበዓላት ቀናት በታላቁ የገበያ ቦታ መርካቶ …

0
1565

መርካቶ በአፍሪካ ትልቁ ክፍት የገበያ መዓከል ነው፡፡ ይህ የገበያ ቦታ ከለሌቲ እና ከእሁድ በስተቀር በሰዎች የተጨናነቀ እና የገበያው ጋጋታም ሞቅ ደመቅ ያለ ቢሆንም በበዓላት ወቅት ሲሆን ደግሞ የመርካቶ ድባብ ለየት ያለ ይሆናል፡፡

በርካታ ባለቅኔዎች ቅኔ የተቀኙለት መርካቶ የበዓላት ቀናት ትርምስ የተለየ መልክ እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡

በመርካቶ የማይሸጥ ነገር ይገኛል ማለት ዘበት ነው፡፡ በበዓላት ወቅት ሲሆን ደግሞ ሻጭ እና ገዢ ቁጥራቸው ይጨምራል ፤ የገበያውም ሁኔታ የምግብ እና ምግብ ነክ እቃዎች እና የቤት ቁሳቁሶች  ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ፡፡

ገበያው ለሀገሪቱ ብሎም ለአፍሪካ ትልቁ ገበያ እንደመሆኑ መጠን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ የትኛውም የሀገሪቱ ጫፍ ሸቀጥ ይሄዳል ይመጣል፡፡

የመርካቶን የገበያ የበዓል ድባብ በተመለከተ አርቲስት ጋሽ አበራ ሞላ ፣ ብርሃኑ ሰሙ እና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሰጡትን የተለያዩ አዝናኝ አስተያየቶች እና የትበብ ስራዎች በዚህ በኢቢሲ ቪድዮ ላይ መከታታተል ይችላሉ፡፡

READ  የገና ጨዋታ እና ታሪካዊ ዳራው …

NO COMMENTS