9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ከትናነት በስተያ በተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል፡፡

0
1097

9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ከትናነት በስተያ  በተለያዩ ከተሞች ተካሂዷል፡፡

ከትናነት በስተያ በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከተማ ድል ቀንቶታል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም አዲስ አበባ ከተማን የገጠመው ፋሲል ኤዶም ኮድዞ በ6 እና 32ኛው ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠራቸው ግቦች 2 ለ 0 ረቷል።

መከላከያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለምንም ግብ ተጠናቋል

ትላንት አዲስ አበባ ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ሃዋሳ ላይ ሃዋሳ ከተማ እና ወላይታ ዲቻ ተገናኝተው 3 እኩል በሆነ ውጤት ጨዋታቸውን ጨርሰዋል፡፡

ጅማ ላይ ጅማ አባ ቡና ከሲዳማ ቡና ተጫውተው ባለ ሜዳው ጅማ አባ ቡና ጨዋታውን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አርባ ምንጭ ላይ ተደረገው የአርባ ምንጭ ከተማና ደደቢት ጨዋታ ደግሞ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን አሸንፏል፡፡

 

ጊዮርጊስ በአዳነ ግርማ፣ ሳልሃዲን ሰዒድ እና ራምኬል ሎክ ጎሎች ነው 3 ለ 0 ማሸነፍ የቻለው፡

ወልድያ ከተማ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን ዛሬ አርብ በመልካ ቆሌ ያስተናግዳል።

READ  አለማቀፉ የእግር ኳስ ማህበር /ፊፋ/ በዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉ ሀገራት ቁጥር ወደ 48 እንዲያድግ ወስኗል

NO COMMENTS