በአዲስ አበባ ባለፉት 20 ቀናት በተደረገ ፍተሻ 263 አሽከርካሪዎች ጠጥተው ተገኝተዋል

0
1841
ጠጥተው የሚያሽከረክሩ
ላለፉት 20 ቀናት በትራፊክ ፖሊስ አባላት በ8 ሺህ 300 በላይ አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻም 263 አሽከርካሪዎች ጠጥተው ተገኝተዋል ነው ያለው ኮሚሽኑ።

ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን የአልኮል መጠን የሚለካው መሳሪያ በአዲስ አበባ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ሆኗል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው መሳሪያው ከታህሳስ 7 2009 ዓ.ም ጀምሮ ነው በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የሆነው።
ላለፉት 20 ቀናት በትራፊክ ፖሊስ አባላት በ8 ሺህ 300 በላይ አሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ፍተሻም 263 አሽከርካሪዎች ጠጥተው ተገኝተዋል ነው ያለው ኮሚሽኑ።

የኮሚሽኑ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ግርማ ተሰማ ለፋና ብሮደካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ ከተገኙት ውስጥ 144 የሚሆኑት ህጉ ካስቀመጠው የአልኮል መጠን በላይ ጠጥተው የተገኙ ናቸው።

ቁጥጥሩ የተካሄደው በቀንና በሌሊት መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ግርማ፥ 113 በሌሊት ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የተገኙ ሲሆን
የተቀሩት 150 አሽከርካሪዎች ደግሞ ቀን ላይ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የተገኙ ናቸው።

ጠጥተው ከተገኙት አብዛኛዎቹ የላዳ ታክሲ እና የኮድ 2 አውቶሞቢል አሽከርካሪዎች መሆናቸውንም ነው ኮማንደር ግርማ የተናገሩት።
የአልኮል መጠን መቆጣጠሪያ መሳሪያው የሙከራ ጊዜው ሲጠናቀቅ በህጉ የተቀመጠው ቅጣት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የላዳ ታክሲዎች በዚህ ያህል ደረጃ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸው ፤
አግባብ እንዳልሆነ የሚገልጹት ኮማንደር ግርማ በህዝብና በመንግስት የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
መጪውን የገና በዓል አስመልከቶም ህብረተሰቡ በሚዝናናበት ጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ሀላፊው አሳስበዋል።

በቀጣይ በሚኖሩ የቁጥጥር ሂደቶች ጠጥተው የሚገኙ አሽከርካሪዎች መንጃ ፈቃዳቸውን እስከመንጠቅ የሚደርስ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አውቀው መጠንቀቅ ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት።

አሁን ላይ ጠጥተው የተገኙ አሽከርካሪዎች ምክርና ግንዛቤ ተሰጥቷቸው በሌላ ተሽከርካሪ እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ኮማንደር ተሰማ፥ የሙከራው ጊዜ ሲጠናቀቅ ግን የቅጣት ህጉ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።

READ  ከሃላፊነት የሚነሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያገኟቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የተዘጋጀው አዋጅ ሊሻሻል ነው

ለመጀመሪያ ጊዜ ጠጥተው የተገኙ አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቅጣት የሚጣልባቸው ሲሆን፥ በድጋሚ ጠጥተው የሚገኙት ደግሞ የመንጃ ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ።

በአዲሱ የአልኮል መጠን መቆጣጠሪያ መሳሪያ አጠቃቀም ዙሪያ እስካሁን 120 የትራፊክ ፖሊስ አባላት ስልጠና መውሰዳቸውን ኮማንደር ግርማ ገልፀዋል።fanabc

NO COMMENTS