የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ለ 10ሺህ ታራሚዎች ምህረት ሰጠ

0
558
የኦሮሚያ ክልል ለ 10ሺህ ታራሚዎች ምህረት ሰጠ
የተቃዋሚው መድረክ መሪ በፖለቲካ የታሰሩ እንዲፈቱ ሲጠይቁ የክልሉ መንግስት በበኩሉ በፖለቲካ የታሰረ ሰው የለም ብሏል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ መስፈርቱን ላሟሉ ላሏቸው 10 ሺህ እስረኞች ምህረት ሰጡ፡፡

የተቃዋሚው መድረክ መሪ በፖለቲካ የታሰሩ እንዲፈቱ ሲጠይቁ የክልሉ መንግስት በበኩሉ በፖለቲካ የታሰረ ሰው የለም ብሏል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ለማ መገርሳ መስፈርቱን ላሟሉ ላሏቸው 10 ሺህ እስረኞች ምህረት ሰጡ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ ከ 36 ማረሚያ ቤቶች የእርምት ቆይታቸው ተገምግሞ መስፈርት አሟልተዋል ለተባሉ ታራሚዎች ምህረት የተሰጠ ሲሆን ታራሚዎቹ ዛሬ ተፈተው ወደማህበረሰቡ ይቀላቀላሉ ተብሏል፡፡

ይህን ምህረት በሚመለከት የተጠየቁት የተቃዋሚው መድረክ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምህረቱ ገንቢ እርምጃ ቢሆንም በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ከተፈለገ የተቃዋሚ ፖለቲካ ቡድኖች አባላትና በፖለቲካ የታሰሩ ሁሉ ይፈቱ ሲሉ ለቪኦኤ አማርኛው ዝግጅት ተናግረዋል፡፡
በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ይፈቱ ያሉት ፕሮፌሰር በየነ በወንጀል ድርጊት ሳይሳተፉ መንግስትን በመቃወማቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ በርካታ ሰዎች አሉ ብለዋል፡፡ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸው በክልሉ በፖለቲካ ጉዳይ የታሰረ ሰው የለም ብለዋል፡፡

መደበኛ ምህረት እንጂ ከወቅታዊ ጉዳይና ከምንም ሁኔታ ጋር አይገናኝም ሲሉ ምህረቱን የገለጹት አቶ አዲሱ ምህረቱ የተወሰኑ ታራሚዎችን ብቻ እንደሚያጠቃልል አስረድተዋል፡፡ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ ማጣሪያን መሰረት በማድረግ ፕሬዘዳንቱ በህግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት ምህረቱን ሰጥተዋል፡፡ ግልጽ መስፈርት ወጥቶ የተካሄደ ምህረት ነው፡፡ ተፈቺዎቹ ከማህበረሰቡ ጋር ቢቀላቀሉ የወንጅል ስጋት እንደማይሆኑ ታምኖበትና ተገምግመው ይገባቸዋል ለተባሉት ብቻ ነው ምህረት የተሰጠው፡፡

ከዚህ ቀደም ዘመን መለወጫ ላይ ቢደረግም ምህረት መስጠት የግዴታ በዚህ ጊዜ ብቻ ይሁን የሚል ህግ ባለመኖሩ የክልሉ መንግስት ምህረት አድርጓል በማለት አቶ አዲሱ የይቅርታውን አግባብነት በሰፊው አብራርተዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ባለፈው አመት ዘመን መለወጫ ላይ 4 ሺህ ታራሚዎችን ፈትቷል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ምህረት ደረገ ሲሆን ዘመን መለወጫ ላይ 5 ሺ አሁን ደግሞ 10ሺህ በይቅርታ ለቋል፡፡

READ  የጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ተጠናቀቀ

Oromia region pardoned 10,000 prisoners

By Elias Meseret

(DireTube News. Addis Ababa, Ethiopia) – Ten thousand prisoners have been pardoned in the restive Oromia region of Ethiopia, the state broadcaster EBC reported on Wednesday evening. The pardon came amid a State of Emergency in the country that has led to the arrest of several thousands of others across the nation.

“The Oromia region’s President has pardoned prisoners that have chronic illness, are old and have family and children,” the broadcaster said adding that the latest pardon doesn’t include that are sentenced for rape, human trafficking and corruption.

On 21 October, Ethiopia pardoned other 9,800 suspects that were nabbed under the country’s State of Emergency. Authorities said at the time that another 1,449 will be held and charges will be filed against them for their roles during the violent protests across the Oromia and Amhara regions at the beginning of October.

“We welcome the release of the prisoners,” Mualtu Gemechu of the opposition Oromo Federalist Congress told the Associated Press and DireTube reporter Elias Meseret. “But at the same time people are being detained en masse across Oromia. The arrests have become so severe that prison facilities are now at full capacity so people are being held at private residences and government facilities.”

READ  ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ፕሮግራሞች የተጨመረም ሆነ የተቀነሰ ዓመት የለም

Mulatu said his rough estimates are some 60,000 to 70,000 people were detained in recent months across the Oromia region. But he said almost all his party’s offices in the region are now closed by authorities so they couldn’t compile the right figures.

The Ethiopian government is announcing that it has allocated hundreds of millions of dollars to create jobs for the youth across the country. Thousands of public servants have also been dismissed and hundreds of others were detained in the past few weeks for maladministration and corruption.DIRETUBE NEWS

NO COMMENTS