ኦፍና አማኑኤል-ገና በቀሳውስቱ የሚደምቅበት የመርሐቤቴ መገለጫ

0
417
ኦፍና አማኑኤል-ገና በቀሳውስቱ
ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ሰሜን ሸዋ በምናብ ሊወስደን ነው፤ ትናንት ጀምሮ የሚደምቀው ኦፍና አማኑኤል ዛሬ አማኑኤል ከልደት በዓል ጋር አብሮ የሚከብርበትን ታሪካዊው ስፍራና የልደት በዓል ኩነቱን እንዲህ ይተርክልናል፡፡

ኦፍና አማኑኤል-ገና በቀሳውስቱ የሚደምቅበት የመርሐቤቴ መገለጫ፤(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ሰሜን ሸዋ በምናብ ሊወስደን ነው፤ ትናንት ጀምሮ የሚደምቀው ኦፍና አማኑኤል ዛሬ አማኑኤል ከልደት በዓል ጋር አብሮ የሚከብርበትን ታሪካዊው ስፍራና የልደት በዓል ኩነቱን እንዲህ ይተርክልናል፡፡) (ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ)

ላሊበላ ልደት በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ ሀገር ያቋረጡ፣ ሜዳ የሰነጠቁ፣ ዳገት ቁልቁለት የወጡ ምዕመናን ደብረ ሮሐ ደርሰዋል፡፡ ነገ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ብቻ አይደለም፡፡ ቅዱስም ንጉሥም የሆነው የላሊበላ ልደትም ነው፡፡ እናም ገና ይህቺን ምድር ሲረግጥ ላል ይበላል ተባለለት የተባለውን ታላቅ ንጉሥ ጥበብ የሚያደንቁ ዘመን ከማይሽረው ውቅር ስራዎቹ ጋር የልደትን በዓል በላስታ ያደምቁታል፡፡

ላሊበላ የራቃቸው ደግሞ ሰሜን ሸዋ ገብተዋል፡፡ ኦፍና አማኑኤል መርሐቤቴ ምድር የሚገኘው ታሪካዊ ስፍራ፤ ይህ ቦታ በአብረሐ ወ አጽበሐ የተተከለ ነበር፡፡

ዛሬም በድንቅ ሁኔታ ምድር የተፋችው የፍርስራሽ ቅሪት እና የአሁኑን ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ሲቆፈር የተገኙት ቅሪቶች የኦፍና አማኑኤልን ገናናነት ያሳያሉ፡፡ ኦፍናን ማየት ዛሬ ነው፡፡ መርሐቤቴዎች ነገን ዛሬ ይጀምሩታል፡፡ የደብረ ታቦር ኢየሱስ ተራራ ጨለማው በጧፍ ብርሃን እንደሚወግግ ሁሉ መርሐቤቴም ከልደት በዓል ጋር በእጅጉ የሚቆራኝ ገና የሚደምቅበት ታሪካዊ ስፍራ አለው፡፡ ሰሜን ሸዋ…..የገናን በዓል ከነሙሉ ክብሩ ኦፍና አማኑኤል መታደም ይቻላል፡፡

መርሐ ቤቴ መርሐ እና ቤቴ ከሚሉ ሁለት የግዕዝ ቃላቶች የተመሰረተ ሲሆን መርሐ ማለት መራኝ ወይም አደረሰኝ ቤቴ ማለት ደግሞ መኖሪያዬ፣ ቤቴ ማለት ነው ይላሉ አበው፤ ስለዚህ መርሐቤቴ ማለት ወደ ቤቴ መርቶ አደረሰኝ ማለት ነው፡፡

ይሄ ስም በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዘመነ አብርሐ ወ አፅብሀ (ኢዛናና ሳኢዛና) የክርስትና እምነትን በሚያስፋፉበት ጊዜ በአሁኑ ሰዓት «ኦፍና» እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ሲደርሱ ቦታው ከመናገሻቸው አክሱም ጋር ተመሳስሎ ስላገኙት ወደ ቤቴ መራኝ፣ ከቤቴ አደረሰኝ ሲሉ መርሐ ቤቴ የሚለውን ስያሜ እንደሰጡት አባቶች ትውፊታቸውን ጠቅሰው ያስረዳሉ፡፡

READ  አሸተን ማርያም-የነአኩቶ ለአብ ድንቅ ስራ

የት መሰላችሁ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ዓለም ከተማ ከምትባለው እና 180 ኪሎ ሜትር ርቃ ከምትገኘው የመሬዎች መዲና አቅራቢያ ነው፡፡ በእነ አቡነ ሰላም ከሳቴ ብርሃን መሪነት በነገስታቱ በአብርሃ ወአፅብሃ (ኢዛና ና ሳይዛና) ዘመን የተተከለው ኦፍና በአማራ ሳይንት ከምትገኛው ከተድባበ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቀጥሎ የተተከለ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ኦፍና አማኑኤል የተሰራበት ስፍራ ከቤተልሔሟ ክርስቶስ የተወለደባት ስፍራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የቦታ አቀማመጥ አላት የሚለው የኦፍና ታሪክ በዚህ ሳቢያም ነው በቅዱስ አማኑኤል ስም ቤተ ክርስቲያን የተተከለባት፡፡

ቀድሞ ቤተክርስቲያኑ የተሰራበት ቦታ መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ ወጣ ገባ በመሆኑ እንዲስተካከልና ከፍ ብሎ እንዲታይ ጠንካራ አፈር ከሚገኝበት ከተለያየ ቦታ በምእመናን ሸክም እየተጋዘ ተደልድሎ የተሰራ መሆኑ ይነገራል፡፡ ዛሬም በአራቱ ማእዘን የለው የአፈር አይነት የተለያየ መልክ አለው፡፡ ነገስታቱ በወቅቱ በምን እንደሰሩት ባይታወቅም ኖራ መሰል ቁሱና የቤተ ክርስቲያኑ ጌጥ የነበረው እብነ በረድ ለዘመናዊው ህንፃ ስራ ግንባታ በተደረገ ቁፋሮ የተገኙ ቅሪቶች ናቸው፡፡

በነገስታቱ አብርሃ ወአጽብሃ በተሰራው በዚህ በኦፍና አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ጥንት የተሰሩ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በጦርነት ተቃጥለው ወድመዋል፡፡ ኦፍና አማኑኤልም ይሄ አደጋ ገጥሞት ዛሬ ጥንታዊው ቅርስ ቅሪት ሆኗል፡፡

ዛሬ ታህሳስ 28 ነው ኦፍና በድምቀት ይነገሳል፡፡ የገና በዓል ለሁለት ቀናት በደመቀ ሁኔታ የሚከበርበት ስፍራ ነው፡፡ ጥንታዊውን የገና ጨዋታ ለመመልከትና እድሜ ጠገብ ባለታሪክ የገና ጨዋታ መጫዎቻ “ሩርት” መመልከት ከፈለጉ ለአዲስ አበባ ማን እንደ ኦፍና ቀርቦ…DIRETUBE NEWS

NO COMMENTS