አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ በጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው

0
1696

አርቲሰት ሙሉአለም ታደሰ በጄቲቪ በሚተላለፈው ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው ቀርባ ነበር፡፡

በልጅነቷ ሀረር በሚገኝ የካቶሊክ ገዳም ውስጥ መማሯን እና ይህ የህወት ዘመኗ ለእርሷ ወርቃማ ግዜ እንደነበር ተናግራለች፡፡

የገና በዓልን የሚያከብሩበት መንገድም እንደ አሁኑ የገና አባት እና የገና ዛፍ የሚባሉ ነገር ሳይሆን በረት በመስራት ህጻናት በጣሳ የተለያዩ ተክሎችን ተክለው በተሰራው በረት ውስጥ በማስቀመጥ ነበር ብላለች፡፡

የሀረር ከተማ ልጅ መኋኗ አሁን ላላት ባህሪ ያደረገባት ተጽእኖ ምን እንደሆነ ለቀረበላት ጥያቄ ስትመልስ የሀረር ልጅ መሆኔ ከተለያዩ ሃይማኖት ካላቸው ሰዎች ጋር ተቻችሎ የመኖር ባህልን እንደዳብር አድርጎኛል ብላለች፡፡ የተለያዩ ሃይማኖት ያላቸው ወዳጆም አሉኝ ብላለች፡፡

በልጅነት ዘመኗ ‹‹ቀልቃላ›› የምትባል አይነት እንደነበረችም ተናግራለች፡፡

ሰባተኛ ክፍልንም በሶማሌ ወረራ ምክንያት አዲስ አበባ በሚገኘው ጆን ኦፍ ኬኔዲ ትምህርት ቤት መማሯን እና የሀረር የአነጋገር ዘይቤዋ በአዲስ አበባ ሌሎችን የሚያዝናና እና የሚያስቃቸው አንደነበር ታስታውታለች፡፡

በልጅነት ዘመኗ ከወንዶች ጋር እግር ኳስ ትጫወት እንደነበር በትምህርቷም የተነገራትን ቶሎ የመቀበል ችሎታ እንዳላት ተናግራለች፡፡

ወደ ሃይስኩል ስትደርስም ቦሊቦል ፣ ዋና እና ሌሎች ስፖርቶችን ታዘውትር እንደነበር ብሎም ትምህርት ቤቷን በቦሊቦል ስፖርት መወከሏን አስታውሳለች፡፡

የሃይስኩል ትምህርቷን መታህራ ከተማ እንደተማረች ወደ እዛም የመጣችው የልጇን አባት ተከትላ እንደሆነ እና ልጇን የወለደችውም የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለች መሆኑን ገልጻለች አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ፡፡

በልጅነቷ ባደገችበት ገዳም ውስጥ በገዳሙ ለሚገኙ ደናግላን መንፈሳዊ ቲያትር ታቀርብ እንደነበር እና ይህም ለቲያትር ህይወቷ እንደጅማሮ እንደምታየው የምትገልጸው አርቲስት ሙሉአለም አስራ ሁለተኛ ክፍልን አጠናቃ የተለያዩ ትምህርቶች ብትማርም የውስጥ ስሜቷ ባለመሆኑ በመተሃራ በሚሰጥ የቲያትር ኮርስ እድል አግኝታ ቲያትር ለመማር ችላለች፡፡ ‹‹ፍቅር በተናጥል›› የሚል ስራም እዛው የቲያትር ኮርስ እየወሰደች ባለችበት ትምህርት ቤት መስራቷ ይህም ብሄራዊ ቲያትር ለመግባቷ መንገድ መፍጠሩን ተናግራለች፡፡

READ  የጥርስ ሳሙና ጥርስ ከማጽዳት ባለፈ የሚሰጣቸው 10 ጥቅሞች

የመመረቂያ ስራችን በዋና ገጸ ባህሪ በመስራት በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ መጥቻለሁ ብላለች፡፡

አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ እና ጆሲ በሌሎች ጉዳዮች ላይም ቆይታ አድርገው ነበር ሙሉ ቪደዮውን መከታተል ይችላሉ፡፡

NO COMMENTS