ታዋቂ ድምጻዊያን ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል

0
962

ታዋቂ ድምጻዊያን ለገና በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል – የጌታ እና የሎሌ ታናሽና ታላቅነት በገና ጨዋታ ኤሰራም እንደውም ከነ አባባሉ አሲና  ገን በገና ጨዋታ እዮሀ አሲናገናዬ አሲና ገን አይቆጡም ጌታ አይደል የሚባለው፡፡ ጌቶች ሜዳ ውርደው  በገና ከሎሌዎቻቸው ጋር የገና ጨዋታ ሲጫወቱ በሎሌያቸው ለሚደርስባቸው እርግጫም ይሁን ጡቻ ቂም መያዝም ሆነ መቆጣት የማይታሰብ ነው፡፡

ሀይማኖታዊውን ይዘት ስናየው የቤተክርስትያን አስተምሮት ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከሰዎች ጋር መደባለቁን ይነግረናል፡፡

እንዲህ እንዲህ እየሆነ ታዲያ የግሪጎሪያንን ካላንደር መከተል የጀመሩት ምዕራባውያን በእነሱ አቆጣጠር ዲሴምበር 25 ላይ የገና በዓላቸውን ሲያከብሩ በኢትዮጵያችን ደግሞ የኖረውን የጁሊያን ካላንደርን በመከተል ታህሳስ 29 ቀን ከሁለት ሳምንታት በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች  ዘንድ የክርስቶስ ልደት በድምቀት ይከበራል ፡፡

በዓሉን የምታከብርበት የራሷባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ዘውግ ያለት ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የምዕራባውያኑ ባህል እየተበረዘበት የገና ዛፍ እና የገና አባት መለመድ ከጀመሩ ሰንበት በሏል ፡፡

ያው አሁንም ያለነው ወረሀ ታህሳስ መገባደጃ ላይ አይደል ቅዳሜ ለሚከበረው የክርስቶስ ልደት ማለትም የገና በዓል ድሬቲዩብ ከጥቂት ድምፃውያን ጋር ቆይታ አርጓል የልጅነት ጊዜ የገና በዓል ትዝታቸው ምን ይመስል ነበር የባህሉን የገና ጨዋታስ ተጫውተው ይሆን ወይንስ እነሱም በገና አባት ነው ያደጉት ..፡፡

እንግዲህ እኛም በዓሉ የሰላም የፍቅር አውዳመት እንዲሆን በሀገር ውስጥም ከውጪም ላላችው ወዳጆቻችን ተመኘን

READ  በኮምፒውተሮቻችን እምብዛም የማንጠቀምባቸው ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የኤፍ ቁልፎች እና ጠቀሜታዎቻቸው፡፡

NO COMMENTS