ስለ ዘርፈ ብዙው ባለሞያ አበበ ባልቻ ያልተሰሙ እና አስገራሚ አስር እውነቶች

0
4709

በቲያትር ፣ በፊልም ፣ በሬድዮ ስራዎቹ እና በተማረበት የጥብቅና ስራው የሚታወቀው አበበ ባልቻ የበርካታ ሙያዎች ባለቤት እና ተወዳጅ አርቲስት ለመሆን የበቃ አንጋፋ ባለሞያ ነው፡፡

ኢትዮ ታይም የተባለ መረጃ አቅራቢ ስለ አበበ ባልቻ አስር እውነቶች በሚል መረጃ አቅርቧል፡፡ እኛም በሚከተለው መልኩ አቅርበንላችኋል፡፡

  1. አበበ ባልቻ የተወለደው በ1948 እንግሊዝ ኢምባሲ ውስጥ ነው፡፡
  2. ከአንደኛ እስከ አስራሁለተኛ ክፍልም በኮከበ ጽባህ ትምህርትቤት ተምሯል ይላል መረጃውን ያጠናቀረው ኢትዮ ታይም
  3. አበበ የህግ ምሩቅ እና ዋናው ሞያውም ጥብቅና መሆኑም በመረጃው ተጠቅሷል
  4. የከፍኛ ትምህርቱን ሲከታተል ቅርጫት ኳስ ይወድ እና ያዘውትርም ነበር
  5. የእውቋ ጋዜጠኛ እና የሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ባለቤት የመአዛ ብሩ የትዳር አጋር ሲሆን አበባ ባለቤቱን ጓደኛዮ እና የልጆቼ እና ሲል ይገልጻታል
  6. በመረጃው አበባ ባልቻ በልጅነቱ ከአበበ ቢቂላ እና ከማሞ ወልዴ ጋር የመሮጥ እድል እንዳጋጠመው ተመልክቷል
  7. ለመጀመሪያ ግዜ የተጫወተው ቲያትር ኦቴሎ ሲሆን በወቅቱ እድሜው 25 ዓመት ነበር፡፡ ይህን ተውኔት ለመተወን የመረጡት በቅርቡ በሞት ያጣናቸው ጋሽ አባተ መኩሪያ ነበሩ
  8. በርካቶች የአበበ የመጀመሪያ የትወና ስራ የሰው ለሰው ድራማ እነደሆነ ያምናሉ
  9. ስለ ቀድሞው መስሪያ ቤቱ አውራ ጎዳና አውርቶ አይጠግብም
  10. በዋሽንግተን ፣ በኒውዮርክ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የትወና ስራውን አቅርቧል
READ  ውዝግቡ ያየለው የኢትዮጵያ ፊልም ሠሪዎች ማህበር

NO COMMENTS