የፌስቡክ ፈጣሪና ሀላፊ ማርክ ዙከርበርግ በመጨረሻ ሀይማኖት አለኝ አለ

0
9062
ማርክ ዙከርበርግ
በቢሊዮን የሚቆጠሩ የአለም ህዝቦችን በማህበራዊ ሚዲያ ያስተሳሰረው የፌስቡክ ፈጣሪና መሪ ማርክ ዙከርበግ ሀይማኖት ያለው መሆኑን ተናገረ፡፡

በቢሊዮን የሚቆጠሩ የአለም ህዝቦችን በማህበራዊ ሚዲያ ያስተሳሰረው የፌስቡክ ፈጣሪና መሪ ማርክ ዙከርበግ ሀይማኖት ያለው መሆኑን ተናገረ፡፡ ከዚህ ቀደም በፌስቡክ የግል ማህደሩ ላይ ሀይማኖትን በሚጠይቀው ዝርዝር ላይ ሀይማሎት የሌለው ሰው መሆኑን በመጻፍ የሚታወቀው ዙከርበርግ አሁን ግን ሀይማኖት ጠቃሚ ስለመሆኑ መመስከሩና ሀይማኖት ያለው መሆኑን መናገሩ ተዘግቧል፡፡

እራሱን ጨምሮ ባለቤቱ፣ ሴት ልጁና ውሻው ለመላው ክርስቲያን ተከታዮቹ ለገና በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እናስተላልፋለን ሲል ፌስ ቡክ ገጹ ላይ ያሰፈረው ዙከርበርግ ከመቼ ወዲህ ሀይማኖተኛ ሆንክ የሚል አስተያየት ሰጪዎች ገጥመውት ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ ከአይሁድ ቤተሰብ መወለዱንና አይሁድ ሆኖ ማደጉን ለተከታዮቹ የተናገረው ዙከርበርግ በጥያቄ ተሞልቼ የኖርኩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ አሁን ግን ሀይማኖት እጅግ ጠቃሚ ነገር መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ በማለት አሁን ላይ የሀይማኖት ተከታይ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ሰሞኑን በወጡ ሌሎች ዜናዎች ላይ ዙከርበግርግ ወደፖለቲካውም ለመግባት ይፈልጋል የሚሉ መረጃዎች ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ ወጣቱ ቢሊየነር ለአሜሪካ ፖለቲከኞች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ፣ የቻይና ቋንቋን መማሩ እንዲሁም በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች በመዘዋወር የሰዎችን አስተያየት ለመስማት መሞከሩ ሁሉ ለፖለቲካ ዝንባሌ አለው ከሚለው ጉዳይ ጋር ሲያያዝ ነው የሰነበተው፡፡

ይህን ተከትሎ ዙከርበርግ በይፋ የተናገረው ነገር ባይኖርም አሁን ካለበት ሀላፊነት በተጨማሪ ፖለቲካን ደርቦ ይሰራል የሚለው ጉዳይ የማይመስል አስተያየት መሆኑን ነው የቅርብ ሰዎቹ የተናገሩት፡፡
huffingtonpost

READ  ኢትዮጵያና ቱርክ አምስት የትብብር ስምምነቶች መፈራረማቸው ተዘገበ

NO COMMENTS