አንበሳ አውቶቡስ ከ277 በላይ አውቶብሶችን ጨረታ አወጣ

0
1825
አንበሳ አውቶቡስ
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ277 በላይ የሆኑ አውቶብሶችን ለጨረታ ያወጣ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመለከተ።

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ277 በላይ የሆኑ አውቶብሶችን ለጨረታ ያወጣ መሆኑን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመለከተ። ይህም የመጀመሪያ ዙር ጨረታ መሆኑ ታውቋል።

ድርጅቱ ለጨረታ ያቀረባቸው የቀደሙትና ከውጭ ተገዝተው በመግባት ለረዥም ጊዜ አገልግሎት የሰጡት እንደዚሁም ከዓመታት በፊት በብረታብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ተገጣጥመው ለድርጅቱ የቀረቡ አውቶብሶች መሆናቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ድርጅቱ ከአንድ ሺህ በላይ አውቶብሶች ያሉት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በየቀኑ የሚያሰማራቸው አውቶብሶች ቁጥር 460 ያህል ብቻ ናቸው።

ድርጅቱ በከተማው አስተዳደር በኩል ሌሎች ተጨማሪ አውቶብሶችን ከውጭ ለማስገባት እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል። በዚህ ዓመትም አንድ መቶ አውቶብሶችን ለማስገባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ተብሏል።

ድርጅቱን አቅሙን ለማሳደግ የመዋቅር ለውጥ፣ የሰራተኛ ምድባ እና የሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ታውቋል። አሰራሩንም ለመለወጥና የአውቶብሶችን ስምሪት ከማዕከል ለመቆጣጠር የሚያስችል ስራም ከአለም ባንክ በብድር በተገኘ ገንዘብ እየተሰራ መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አዳዲስ አውቶብሶችን ለመግዛት የስራ ኃላፊዎች ውጭ ሀገራት በመሄድ የምልከታ ስራ የሰሩ መሆኑ ታውቋል። ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በኩል የተገጣጠሙ ከ5 መቶ ያላነሱ አውቶብሶችን ተረክቦ ሲሰራ የቆዩ ሲሆን ባለፉት ጊዜያት ከ100 በላይ አውቶቡሶች በቴክኒክ እና የመለዋወጫ ችግር ገጥሟቸው የቆሙበት ሁኔታ ነበር።
sendeknewspaper

READ  ሞባይል ስልክ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አሻሽሏል ተባለ

NO COMMENTS