ታንዛኒያ ድሮኖችን ለደምና ለህክምና ቁሳቁሶች ማጓጓዣነት ልትጠቀም ነው ተባለ

0
687
ታንዛኒያ ድሮኖችን ለደም
አነስተኛ በራሪ አካላት ወይም ድሮኖች በተለያዩ ሀገራት በሙከራ ደረጃ ለእቃ ማጓጓዣ ንግዶች ጥቅም ላይ ፈመዋላቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ታንዛኒያ በዚህ ዘርፍ አዲስ ነገር ለመጀመር ማቀዷ ተሰምቷል፡፡ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ታንዛኒያ ድሮኖችን ለደምና ለህክምና ቁሳቁሶች ማጓጓዣነት እንደምትጠቀም የሀገሬው የዜና ምንጮች ዘግብዋል፡፡

ሀገሪቱ ለዚህ አገልግሎት አስር ድሮኖችን ዘጋጀች ሲሆን በዶዶማ ግዛት ላሉ 100 የጤና ተቋማት እነዚህ ድሮኖች የደምና የህክምና ቁሳቁሶችን የማቅረብ ስራ ይሰራሉ ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት ድሮኖቹ ከዚህ ቀደም ይህንን መሰሉን መገልገያ ለህክምና ተቋማት ለማመላለስ ይፈጅ የነበረውን አድካሚ አሰራር ያስቀራሉ የተባለ ሲሆን አሰራሩ ፈጣንና ቀልጣፋ በመሆኑ በሰው ህይወት ላይ ይደርስ የነበረውን አደጋም ይቀርፋሉ ታምኖበታል፡፡

በታንዛኒያ ከ 100 ሺህ እናቶች ውስጥ በወሊድ ሳቢያ 432 የሚሆኑት ይሞታሉ፡፡ ከሟቾቹ ውስጥ ደግሞ 80 በመቶዎቹ በደም መፍሰስ አደጋ ይህ እጣ እንደሚገጥማቸው ይነገራል፡፡

አሁን ላይ በፈጣን ሁኔታ ድሮኖቹ ሀደም ለማቅረብ ስለሚስችሉ ይህን ትልቅ ራስ ምታት ሀገሪቱ ለመቅረፍ ማለሟ ታውቋል፡፡ ይህ አዲስ መርሀግብር ደግሞ በበብሪታኒያ አለም አቀፍ ልማት ድርጅት ዲኤፍዲአይ እንደሚደገፍ ተነግሯል፡፡africaupdates

READ  የኢትዮጵያ መንግስት የአምነስቲን ኢንተርናሽናልን አዲስ ሪፖርት ተአማኒነት የጎደለው ሲል ውድቅ አደረገ

NO COMMENTS