ስለ እቴጌ ጣይቱ እና አጼ ምንሊክ እምብዛም ያልተሰሙ እውነቶች ….

0
2103

እቴጌ ጣይቱ በኢትዮጵያ የነገስታት ታሪክ ውስጥ ቆራጥ ጠንካራ እና የተፈተኑ እንደነበሩ በኢትዮ – ጣሊያን ጦርነት ወቅት ያደረጉት የጦረኝነት ጀብዱ ፣ የአመራር ብቃታቸው ፣ ብልህነታቸው እንዲሁም መሰል አስደናቂ ታሪኮች ሲነሱላቸው እና ሲወደሱ ይሰማል፡፡

ስለ አጼ ምንሊክ እና  እቴጌ ጣይቱ ያልተሰሙ እና እምብዛም የማናውቃቸው እውነቶች ምንድናቸው ?  በሚል የተለየዩ እውነቶችን የሚያነሳሳውን እና በአርቲስት መስታወት አራጋው የቀረበውን ፕሮግራም  በሚከተለው መልኩ ያቀረብነው ሲሆን ሙሉ ጥንቅሩንም መከታተል ይችላሉ፡፡

እቴጌ ጣይ አጼ ምኒሊክን ከማግባታቸው በፊት አራት ባሎች ነበሯቸው  የመጀመሪያ ባለቤታቸው ወልደ ማርያም የተባሉ የአጼ ቴዎድሮስ ወታደር እንደነበሩ እና አጼ ቴዎድሮስ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ጉዳይ ባለቤታቸውን እንደገደሉባቸው እና እቴጌንም አስረዋቸው እንደነበር በታሪክ ተጽፏል፡፡

ከዚህ በኋላም ተክለ ጊዮርጊስ የተባሉ ሰውንም አግብተው እንደነበር በታሪክ መጻፉ ተገልጿል፡፡

1873 ዓ.ም ወ/ሮ ጣይቱን ወደ ሸዋ የሚያመጣ ምክንያት ገጠማቸው የሚለው ጥንቅሩ አጼ ቴዎድሮስ ወደ ሸዋ መጥተው ከምንሊክ አባት ጋር ጦርነት ገጥመው የ10 ዓመቱን ምንሊክ መቅደላ ወስደው ባሰሩበት ወቅት የጣይቱ ሁለት ወንድሞች ማለትም ወሌ እና አሉላ ብጡል  ከያኔው ደጅ አዝማጅ ምኒሊክ ጋር አብረው ታስረው ነበር ይላል ጥንቅሩ ፡፡

በ1857 ደጅአዝማጅ ምኒሊክ ከመቅደላ ወደ ሸዋ ሲመለሱ የጣይቱ ወንድሞች ከምንሊክ ጋር ወደ ሸዋ መጥተው ግዛት ተሰጥቷቸው ይኖሩ ነበር ፡፡

በ1873 የወይዘሮ ጣይቱ ወንድም አሉላ ብጡል በመሞታቸው ጣይቱ ከጎጃም ወደ ሸዋ ይመጣሉ፡፡ ጥቂት እንደቆዮም ቀኝ አዝማች ዝቅ አርጋቸው ከተባሉ ሰው ጋር በጋብቻ ይጣመራሉ፡፡

ቀኝ አዝማች ዝቅ አርጋቸው ከሸዋ ንጉስ ምኒሊክ ጋር ለአስራ ስምንት ዓመት የኖሩት የወይዘሮ ባፈና ወንድም ሲሆኑ እዚህ ጋር እጅግ አስገራሚ የሚሆነው አጼ ምንሊክ እራሳቸው የዳሩላቸው መሆኑ ነው ይላል በታሪክ ዳሰሳው፡፡

READ  ከጥር 01 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ፀደቀ

ወይዘሮ ጣይቱ ቀኝ አዝማች ዝቅ አርጋቸውን አግብተው ትንሽ ከቆዩ በኋላ ተፋቱ፡፡ ለአጭር ግዜም ወንዴ የሚባል የበጌ ምድር ሰው አግብተው የነበረ ቢሆንም ብዙም ሳቆዩ ተፋትተዋል፡፡

በመጨረሻም አጼ ምንሊክ የጣይቱ ብጡል አምስተኛ ባል መሆን ቻሉ፡፡

ከጣቱ በፊት የምንሊክ ሚስት የነበሩት ወይዘሮ ባፈና የስምንት ልጆች እናት እና በእሜም ከአጼ ምኒሊክ የእናት ያህል የሚበልጡ እንደነበረም የታሪክ መዝገቦች እንደሚየሳዩ ተገልጿል፡፡

እንደውም የወይዘሮ ባፈና የመጨረሻ ልጅ እድሜ ከአጼ ምንሊክ ጋር ተቀራራቢ እንደነበረም ይነገራል፡፡

የአጼ ምንሊክ እና የወይዘሮ ባፈና የአስራ ስምንት ዓመት የጋብቻ ታሪክ ወይዘሮ ባፈና አካሄዱት በተባለ መፈንቅለ መንስት ምክንያት መቋጨቱ ይወራል፡፡

ሌሎች ተጨማሪ እውነቶችን ከሙሉ ጥንቅሩ ያግኙ

NO COMMENTS