የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከ18 ወራት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተነገረ

0
109

የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከ18 ወራት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።

የነዳጅ ላኪ ሀገራት የነዳጅ ምርትን ለመቀነስ የደረሱት ስምምነት ባሳለፍነው እሁድ ተግባራዊ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው ዋጋው የመጨረው ተብሏል።

በዚህም መሰጠረት አንድ በርሜል ያልተጣራ ድፍድር ነዳጅ በ2 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በዛሬው እለትም በ58.37 የአሜሪካ ዶላር የተሸጠ ሲሆን፥ ይህም በአንድ በርሜል የድፍድፍ ነዳጅ ላይ የ1.55 ዶላር ጭማሪ አሳይቷል።

ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ከሰኔ ወር 2015 ወዲህ ከፍተኛ ጭማሪ መሆኑም ተነግሯል።

የፈረንጆቹን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የነዳጅ ገበያው በትናንትናው እለት ተዘግቶ ነበር የዋለው።

ባሳለፍነው እሁድ ከጀመረው የአውሮፓውያኑ 2017 የመጀመሪያ ቀንም የነዳጅ ላኪ ሀገራት ምርታቸውን ለመቀነስ የደረሱትን ስምምነት የጀመሩበት እለት ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘም እንደ ሩሲያ ላሉ በርካታ የነዳጅ አምራች ሀገራት በቀን ውስጥ ወደ ውጭ ሀገራት የሚልኩትን የነዳጅ መጠን በ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በርሜል ለመቀነስ ተስማምተዋል።

ይህንን ተከትሎም በፈረንጆቹ 2017 የመጀመሪያ የነዳጅ ሽያጭ እለት እንዲህ አይነት ጭምሪ ማሳየቱ፥ ለነዳጅ ላኪ ሀገራት ከፍተኛ ተስፋን የሰጠ መሆኑም ተነግሯል።

READ  Hotels’ Accommodation Charges the Highest in Addis Ababa

NO COMMENTS