ከበርካታ ወራት በኋላ ‹‹ኢትዮጵያዊ ›› የሙዚቃ ኮንሰርት በገና ዋዜማ በላፍቶ ሞል ይካሄዳል

0
304

በሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከተሰማሩ ስኬታማ ሀገር በቀል ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው እና ዘርፉ የበዛ የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው ጆርካ ኤቨንትስ ኦርጋናይዘር ሐበሻ ቢራ ጋር በመተባበር በገና ዋዜማ ከምሽት ጀመሮ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› የተሰኘ ታላቅ የሙዚቃ ድግስ በላፍቶ ሞል ማሰናዳቱን ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫአስታውቋል፡፡

ሶስት ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል በተባለለት በዚህ የገና ዋዜማ ‹‹ኢትዮጵያዊ ›› ኮንሰርት ዝግጅት ላይ ተካፋይ ይሆናሉ ከተባሉት ድምጻዊያን መካከል ታደለ ሮባ ፣ ቤቴ ጂ ፣ ጃኪ ጎሲ ፣ ሳሚ ዳን ፣ ልጅ ሚካኤል፣ ዳዊት ነጋ ፣ ያሬድ ነጉ እና ሳሚ ጎ ተወዳጅ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከወራት በኋላ የሚካሄደውን ይህንን ኮንሰርት  መሃሪ ብራዘርስ ባንድ ፣ ዜማ ባንድ ፣ ወዛመይ ባንድ እና ታዋቂ ዲጄዎች እንደሚያደምቁት በጋዜጣዊ መግለጫው ተብራርቷ፡፡

በዚህ የገና በዓል ‹‹ኢትዮጵያዊ›› የሙዚቃ ኮንሰርት እስከ አምስት ሺህ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃልም ተብሏል፡፡

የዚህ ኮንሰርት የመግቢያ ዋጋ መደበኛው 200 ብር ፣ ለጥንዶች 300 ብር ፣ ቪአይፒ 500 ብር እንዲሁም ትኬቱን ቀድመው ለሚገዙ አንድሺህ ሰዎች በ150 ብር እንደሚሸጥላቸው የኮንስርቱ አዘጋጆች ጠቁመዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ኮንስቱን አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

READ  Ethiopia applauds Sudan for deporting rebel leader, fighters

NO COMMENTS