ኢትዮጵያዊያን ታዋቂ ሰዎች የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊያቋቁሙ ነው ተባለ

0
310

ኢትዮጵያዊያን ታዋቂ ሰዎች ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ የወርልድ ስፔሱ አቶ ኖህ ሳማራና እንዲሁም የሪፖርተሩ አቶ አማረ አረጋዊን የመሳሰሉ ታዋቂ ግለሰቦች በጥምረት ግዙፍ የሚዲያ ድርጅት ሊመሰርቱ መሆኑ ተነገረ፡፡

ሀበሻ ኢንፎርመር የተባለ አምደ መረብ እንዳወራው ከሆነ ድርጅቱ አፍሪካን ሬናይሰንስ ቴሌቪዥን እንደሚባልና ግዙፍ የብሮድካስት አውታር እንደሚሆን ተናግሯል፡፡

የመረጃ ምንጩ እንዳለው ከሆነ እነዚህ ታዋቂ ባለሀብቶች አሁን ላይ ድርጅቱን ለመመስረት የሚስችል አስፈላጊ የፋይናንስና የቴክኒክ ዝግጅትን በማገባደድ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

ውሥጥ አዋቂዎች ነገሩኝ ያለው ዘገባው አፍሪካ ሬናይሰንስ ቴሌቪዥን የተባለው ይህ ተቋም አልጀዚራ ጥሎት የወጣውን በአሜሪካ የሚገኘውን ስቱዲዮ ተከራይቶታል ሲል ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ በቅርቡ ለተወሰኑ የመንግስት እና የግል ተቋማት የቴሌቪዥን ፈቃድ መሰጡ የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያዊያንን መሰረት አድርገው የሚሰሩ እና መሰረታቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ የሆነ በርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

የወሬ ምንጩ የጠቀሳቸው እውቅ ሰዎች በጋራ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደሚያቋቁሙ ከመዘገቡ ውጭ የቴሌቪዥን ጣቢያው ትኩረት እና ሌሎች መረጃዎችን አላካተተም፡፡

READ  የንግድ ውድድር እንዳይኖር በተለያየ መንገድ የሚፈጠሩ ተፅዕኖዎች ነጋዴውን ጭምር እየጐዱ ነው ተባለ

NO COMMENTS