በአማራ ክልል የአስተዳደር ይገባናል ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ነው

0
10310
በአማራ ክልል የአስተዳደር ይ
በአማራ ክልል በተለያየ ጊዜ ተነስተው የነበሩ የአስተዳደር ይገባናል ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ነው፡፡

ደንቢያ ወረዳ ለሁለት ተከፍሏል፡፡በአማራ ክልል በተለያየ ጊዜ ተነስተው የነበሩ የአስተዳደር ይገባናል ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ነው፡፡

ሰሞኑን ዓመታት የፈጀው የደንቢያዎች ወረዳችን ይከፈልልን ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፡፡ ሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘው ደንቢያ ወረዳም ምዕራብ ደንቢያ እና ምስራቅ ደንቢያ በተባሉ ሁለት ወረዳዎች የተዋቀረ ሆኗል፡፡

ቆላ ድባ የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ዋና ከተማ ሆና ስትቀጥል አዲሱ ወረዳ ምዕራብ ደንቢያ ዋና ከተማውን ጯሂት አድርጓል፡፡ ብዙ ጊዜ በበጀት አመቱ መጀመሪያ የሚደረገው ይህንን መሰል አዲስ የአስተዳደር መዋቅር ባልተለመደ መልኩ በበጀት አመቱ አጋማሽ እውን መደረጉ ትንግርት ሆኗል፡፡

ደንቢያ ከዚህ ቀደም በታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የገናና መሳፍንት የይገባኛል ሽኩቻን ያስተናገደ ለም እና ጣና ሐይቅ ዳርቻ የተዘረጋ ምድር መሆኑ ይታወሳል፡፡ DIRETUBE NEWS

READ  በኢትዮጵያ ዳግም ለተከሰተው የድርቅ አደጋ ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገደማ ያስፈላጋል ተባለ

NO COMMENTS