በሆሳእና ከተማ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሊሸጥ የነበረ ከ470 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ ተያዘ ተባለ

0
1027
ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሊሸጥ የነበረ ቅቤ
ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሊሸጥ የነበረ ከ470 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ ተያዘ ተባለ

ፋና ብድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው ከሆነ በሆሳእና ከተማ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ ሊሸጥ የነበረ ከ470 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ጠቅሶ ዘግቧል።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ባደረገው ክትትል ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ ነበር የተባሉ ሶስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም  የከተማዋ ፖሊስ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር መኮንን ገብረ ኪዳን ነግረውኛል ብሏል።

የከተማው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት የጤና እና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ሉበጎ በበኩላቸው፥ ከባእድ ነገር ጋር ተቀላቅለው የሚሸጡ የፍጆታ እቃዎች በጤና ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲሉ አሳስበዋል ብሏል ዘገባው።

በተለይም በበዓል ሰሞን ከባዕድ ነገሮች ጋር ተቀላቅለው ለገበያ የሚቀርቡ የፍጆታ እቃዎች ሊበራከቱ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል ብሏል።

READ  Ethiopian PM says Social Media’s negative impacts simply cannot be ignored

NO COMMENTS